Tuesday, 18 June 2013

ታደሰ የኋላእሸት ማን ነው? እውነተኛ ካህን ወይስ ምን..............

ክፍል አራት
*   በ1982 ዓ.ም አዲስ አበባ፤ ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ በታደሰ እና በአስማረች ዙሪያ ላይ ምን ውሳኔ አስተላለፉ?
* ታደሰ በፍጥነት ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ ሊሰደድ የቻለበት ምክንያት ምን ይሆን?
*  ታደሰ ወደ ኬንያ በሄደበት ወቅት ምን ተፈጠረ?
*  ታደሰ ደብረ ዘይት ያነጸው ሕንጻ ለማን ይሆን?
እንደ ታደሰ ታናሽ ወንድም ይርጋለም የኋላእሸት አገላለጽ….ወንድም ጋሼ (ታደሰ)… እንደዚያ ሲሳደብ እና ሲማታ….አስማረች መጣች….ከዛም ሆድዬ ለምንድን ነው እንደዚህ የምትናገር ውጭ ድረስ እኮ ትሰማለህ አለችው………እኔንም...... ይርግዬ አይዞህ ምን እንደዚህ የሚያስጮህ ነገር ተገኘ አለችኝ?  ታደሰም...... እነዚያ ምቀኞች ናቸው..... ስለ አንቺ እና ስለ እኔ ማንነት እየመረመሩት..... አላት ለአስማረች……. አስማረችም እኔን ምን አልካቸው ብላ ጠየቀችኝ..... እኔም እሷን (አስማረችን) ቤተሰባችን አይደለችም….. በዘራችን ውስጥ እንደዚህ አይነት ስም የለም ብዬ አስረዳኋቸው….የምናገረውን ሳልጨርስ አቋረጠችና....ሌላ የነገርካቸው ነገር የለም አለችኝ…በፍጹም አልኳት….. ስለ እኔና ታደሰ እጮኝነት አልነገርካቸውም አለችኝ፤ በፍጹም አልኳት….ተመስገን….ተናግረህ ቢሆን ኖሮ….እንጇ....በወንድምህ ሕይወት ላይ ነበር የፈረድክበት አለችኝ....ግራ ገባኝ...ቀጠለችና.....ዛሬውኑን ከስራ አፈናቅለኸው ነበር አለችኝ። ከተወሰነ ሰዓት በኋላ የቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ..... የሰበካ ጉባኤ አባላት በሙሉ....... እና የተወሰነ የቤተክርስቲያኒቱ አባላት ሆነው...... ታደሰ ካለበት ቤት መጡ።  እኔም የአመጣጣቸው ሁኔታ አልጣመኝም ነበር…..ወንድም ጋሼም (ታደሰም) እኔን ውጭ እንድቆይ ጠየቀኝ….እኔም ውጭ የወጣሁ መስዬ....... ተደብቄ ነገሮችን ማዳመጥ ጀመርኩ…..ነገሩን ያነሱት የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪው አባት ናቸው….በእድሜ ዘለግ ያሉ አባት ናቸው…..ወንድም ጋሼን (ታደሰን)…እባክህን ልጄ ሳትደብቅ አንድም ነገር ሳትሸሽግ ንገረኝ……እውነታው ምንድን ነው? ምንድን ነው የምሰማው? ለዚህች ልጅ ቀለበት አስረህላታል? ታደሰም…አላሰርኩም እንዳይል...... ከቀለበቱ ስነ ስርዓት ከነበሩት ጓደኞቹ መካከል አንዱ........ ከሳሽ ሆኖ ተገኝቷል….የፎቶ ምስልም አቅርቦለታል….ታደሰ ባላሰበው ሁኔታ ቪዲዮ ቀድተውት ስለነበር…. ይህን ጉድ ለወላጆቼ ሰምተው ከሚያፍሩብኝ......... ምነው አፈር በበላኝ እያለ ሲናገር.... እሰማው ነበር…አስተዳዳሪውም ከዛሬ ጀምሮ ቅዳሴ እንዳትገባ....ንስሐ ግባ....ለምን ፈጣሪህን ትዳፈራለህ? ቤተክርስቲያንን ለምን ታረክሳለህ.....ይህንን ጉዳይ ሕዝብም...... ቤተክህነትም ማወቅ አለበት ይሉት እንደነበር ሰምቻለሁ.....ወንድም ጋሼ ግን ፈጽሞ ይማጸናቸው ነበር.....ሰው አይስማ እባካችሁን....... እኔ ግን ሌላ ስራ እፈልጋለሁ...... ይል እንደነበር አስታውሳለሁ..... ነገር ግን እሁድ እለት..... ሰዎች ከቅዳሴ በኋላ የታደሰና የአስማረችን ጉዳይ...... ወሬውን አስተጋብተውት ስለነበር....... ብዙ ሰው ወንድም ጋሼን ይሰድበው እና ያንቋሽሸው ነበር....ስለዚህም ሸሽቶ ወደ ኬንያ ሄደ.......እኔ ግን የማይገባኝ ነገር ቢኖር.......... ትዳር ከፈጣሪ ነው ይባላል….ወንድም ጋሼም ቀለበት ቢያስር ምንድን ነው ሐጥያቱ? ምንድን ነው ችግሩ፤ በወንድም ጋሼ (ታደሰ) ላይ ስለቀኑበት.....አሳደዱት...... እሱም ተሰድዶ ሔደላቸው……ያው እነሱ ይፈሩ እንጂ እሱስ መጥቶ ሰርጉን ሰርጎ….በክብር አግብቶ ተመልሷል….እንዲያውም ከሃብት ላይ ሃብት ያለው ሰው ሆኗል.....ትእግስትን ቢያጣ እግዚአብሔር አስማረችን ሰጥቶታል፤ እግዚአብሔርም ባርኮታል...ይሄ ሁሉ ሃብት የበረከት ውጤት ነው....ከዚህ እንደዚህ ሲያሳድዱት የነበሩት አሁንም ድረስ እያከኩ ይገኛሉ አለን።  እኛም...... የወንድምህ የታደሰ ታሪክ በጣም ያሳዝናል….ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፏል አልነው….እሱም ወንድም ጋሼ መች በዚህ አበቃ…..ኬንያ ሲሄድ እኮ..... የኔን ታላቅ ወንድም ፍቅረን ከደብረታቦር ወደ አዲስ አበባ አስመጥቶ....... ከአስማረች ጋር እንዲቆይ አድርጓል። ደግሞም ፍቅረን መጀመሪያ ወደ አሜሪካ የወሰደው ወንድም ጋሼ ነው……ፍቅረድንግል አሜሪካ እንዴት ሊመጣ ቻለ አልነው?  ወንድም ጋሼ የጻፈው ደብዳቤ አለ...... ላሳያችሁ ብሎ አሳየን......በዚህ መመሪያ ተከትሎ ነው አሜሪካ የገባው...አሜሪካ (ሲያትል ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሲመረቅ....ዲያቆን ነኝ በልና ደብዳቤ አስጽፈህ ቤተ ክህነት ግባ አለው...ወንድም ጋሼ እንዳዘዘው አደረገ.....ፍቅረንም ያለምንም ውጣ ውረድ ሊውስደው ቻለ አለን። ፍቅረ ድንግል የኋላእሸት ግን ምንም ክህነት እንደሌለው ዓለም ያውቃል።  (ደብዳቤውም በእጃችን ይገኛል....) የታደሰ ታናሽ ወንድም ይርጋለምም እንዲህ አለን...እኔ ተስፋ አልቆርጥም....የማይቻለውን የፍቅረን ጉዳይ አስፈጽሞ የወሰደ የባለቤቱን እና የልጁን ያቅተዋል ብየ አልጠረጥርም...በዚህ ሃብት አለ... አንድ ቀን ፈጣሪ ሁሉንም ሲያስትካክል..... እሷንና ደስታውን ይወስዳቸዋል።  አሁን ለአስማረች እና ለደስታው ደህንነት ሲባል ደብረ ዘይት አንድ ትልቅ ዘመናዊ ባለ 4 ፎቅ ግቢ ሌላኛው ወንድማችን ፍቅረድንግል የኋላእሸትን ልኮ ቤት አሰርቶላቸዋል። ደብረታቦር ያለው ቤትስ ብለን ጠይቀነው ነበር።  ደብረታቦር ሁለት ቤት ሰርቷል….አንደኛው ቤት ለሌላው ወንድማችን ሃላፊነቱን ሰጥቶት ይኖርበታል…… ሌላኛውን ቤት ደግሞ ለወላጆቹ እዛው ደብረታቦር ላይ ገዝቶ አስረክቧቸዋል።  ምንም እንኳ የወንድም ጋሼ ባለቤት አስማረች እና ደስታው ከወላጆቻችን ጋር ቢኖሩም.......... አሁን ግን ደብረዘይት ውስጥ ተሰርቶ ያለቀው ቤት ውስጥ እንዲኖሩ በወንድም ጋሼ ትዕዛዝ ተላልፏል። እኛም ይህን ያደረገበት ምክንያት ምን ይሆን ብለን ጠይቀነውም ነበር…..ይርጋለምም……ስለ ወንድም ጋሼ (ስለ ታደሰ የኋላእሸት) ማንነት ሰው ከጠየቃችሁ አናውቅም በሉ ይለን ስለነበር….እንደዚህ የሚለን ሁኔታዎች ወይም የማይነገረን ሚስጥር ምንድን እንደሆነ ግልጽ ካለመሆኑ የተነሳ..... ነገሩ ግልጽ እስኪሆንልን ድረስ..... የሚመለከተን ነገር የለም ብለን መልስ ከሰጠነው ወዲህ........ነገሮችን ወይም ያለውን ሚስጥር እንኳ ሊገልጽልን ስላልፈቀደ….ባለቤቱን እና ልጆቹን ደብረዘይት ከሰራው አዲስ ቤት እንዲኖሩ አዟቸዋል....ለእኔ ደግሞ ይሄ ነገር ውስብስብ ብሎብኛል...ምኑ እንደሚያስጨንቀውም ግራ ገብቶናል አለን…..ደብረዘይትም ሔደን ቤቱን ተመልክተናል…..መቼስ ይህ ሁሉ ገንዘብ የት እንደመጣ እግዚአብሔር ይወቅ…..በእግዚአብሔር ገንዘብ መቀለድ መልካም አይደለም…..የቤተክርስቲያንን ገንዘብ መዝረፍ እና መመንዘር ውጤቱ መጨረሻው አያምርም…. ያን ሁሉ ቤት እንዴት ሊሰራ ቻለ? አዲስ አበባ ቦሌ ላይ ያለውን ቢዝነስስ እንዴት ሊገዛ ቻለ? ደብረታቦር ውስጥ የጄኔሬተር አከራይ ዋና ቢዝነስ እንዳለውም አረጋግጠናል…ይህ ሁሉ ገንዘብ የት መጣ? …..አንባቢ ግን ይህ ሰው ታደሰ የኋላእሽት ማን እንደሆነ ያስተውል…..ሌባ ከሌብነቱ አይዘልምና ይብቃ እንበል…….ለማንኛውም ይህንን ጉዳይ በተመለከተ እመለስበታለሁ።

በ1982 ዓ.ም ታደሰ የኋላእሸት ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ የሄደበት ወቅት ነበር። በዚያን ወቅት የደርግ ዘመነ መንግስት በወያኔ እየተገረሰሰ የመጣበት ወቅት ነበር። እንደታደሰ አገላለጽ፤ አባቶች ጳጳሳት እሱን ኬንያ አስቀድሞ በመሄድ…. ቦታ አዘግጅቶ እንዲጠብቃቸው በጥብቅ መታዘዙን እና ሄዶም ብቻውን ከኬንያ አምባሳደሮች ጋር በመነጋገር....... ለአቡነ መርቆሬዎስ፤ አቡነ ኤልያስ እና አቡነ ዜና ማርቆስ፤ መልካም ቦታ አዘጋጅቶ እንደጠበቃቸው ሁልጊዜ ሲናገር ይደመጣል።  እውነታው ግን እንዲህ ነው፤ አዲስ አበባ ከሚኖረው አጎቱ ጋርም ስለ ታደሰ ጉዳይ ተነጋግረን ነበር……እንደ ታደሰ አጎት አገላለጽ፦ ታደሰ ወደ ኬንያ ሃገር እንደሌላው ዜጋ ተሰዷል፤ ወደ ኬንያ በተሰደደበት ወቅት…… ታናሽ ወንድሙ ፍቅረ ድንግል የኋላእሸት…… ከእኔ ጋር ለተወሰነ ጊዜ ቆይቷል…… ቢሆንም ታደሰ ከተሰደደ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ….. የተወሰኑ አባቶችም ወደ ኬንያ ሲሰደዱ……ታደሰ እንደሌሎች ስደተኞች…. አብሮ የተሰደዱትን አባቶች ተቀብሏል…… ቢሆንም አዲስ አበባ በነበረበት ወቅት....... አንዲት እናት ልጄ ዘመናዊው ትምህርት አልገባት አለ....... በማለት ታደሰን ታማክረዋለች፤ ታደሰም...... እኔ አንድ ነገር እሰራላትና (እጸ ፋሬስ)...... ትምህርቱ በቀላሉ እንዲገባት ይሆናል የሚል ተስፋ ቃል ሰጣት....ይህንንም ካላት በኋላ....... ደጎስ ያለ ገንዘብ እንድትከፍለው አስጠንቅቆ ነገራት…… እናትየዋም ልጄ ትምህርቱ ገብቷት..... እንደሌላው ሰው ብትመረቅልኝማ....... አንተ ያልከውን ገንዘብ እከፍላለሁ...... ብለው ታደሰና ሴትየዋ ይስማማሉ።  ታደሰም ስራስሩን (ዕጸ ፋሬስ) ወይም እጀሰብ መድሃኒት (በዘልማድ የሃበሻ መድሃኒት ...የጥንቆላ መድሃኒት) ተብሎ የሚጠራውን አድርጎ…ይህን ማታ ከመኝታ በፊት…… እህል በልታ ትጠጣና ተሸፋፍና ትተኛ... ሃይምሮዋ ብሩህ ይሆናል...እመኝኝ ብሎ ለእናትየዋ እጸ ፋሬሱን ይሰጣታል…. እናት ደግሞ..... ልጄ ትምህርቷን ልታጣድፈው ነው እንግዲህ በማለት..... ስለ ልጇ የወደፊት ተስፋዋን ሰንቃ....... ለልጇ  ታደሰ የኋላእሸት የሰጣትን ያንን የቅጠላቅጠል እና የሥራሥር ጭማቂ የመሰለ ነገር ታጠጣታለች……መድሃኒቱም ሃይሉ በዝቶ ስለነበር....... በደሟ ውስጥ ስለሰረጸ (ስለገባ) መርዟት ሞተች……የዚህን ጊዜ ታደሰ በተፈጠረው ክስተት የተነሳ....... የነፍስ ተጠያቂ ከመሆኑ በፊት....... ወዲያውኑ ሳያወላውል ወደ ኬንያ ተሰደደ።  እንደ ታደሰ አጎት አገላለጽ፦ ታደሰን ወደ አዲስ አበባ አምጥቼ ለዚህ ያበቃሁት እኔ ነበርኩ….. ነገር ግን ለብዙ ዘመን በኖርኩበት ሃገር ተዋርጄ...... ተሳቃቄ  እንድኖር አድርጎኛል..... የጎረቤት መዘባበቻ...... መሳቂያ መሳለቂያ አድርጎኛል...ይህ ነገር ከተፈጠረ ወዲህ ብዙ ሰው ለብዙ ጊዜ መጠቋቆሚያ አድርጎኝ ነበር..... እሱ ነው የደበቀው እየተባልኩ መከራየን አይቼ ነበር....... አሁን ግን ሁሉም ነገር ተረስቷል ከ20 አመት በላይ ሆነው...... ለዚህም እግዚአብሄር ይመስገን እኔ ምንም ያደረኩት ጥፋት አልነበረምና አሉን ።  በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን ድረስ እንዳዘነቡትም ነግረውናል…….ነገር ግን ታደሰ በ2006 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ በተመለሰ ጊዜ..... ሰርጉ ሊሆን ሳምንት ሲቀረው….. ታደሰ አጎቱን ስላደረገው ስህተት ይቅርታ እንደጠየቃቸውም አጫውተውናል።  እኛም ታደሰ ወደ ኬንያ ከመሄዱ በፊት..... ለአስማረች ቀለበት አድርጎ እንደነበር........ በታናሽ ወንድሙ በይርጋለም አማካኝነት የተነገረንን ጠይቀነው ነበር።  የታደሰ አጎትም……አወ ቀለበትማ አድርጎ ነበር የሄደው….ነገር ግን በትእግስትዬ ሞት በጣም አዝኖ ነበር…ቢሆንም በአስማረች ዘለዓለም ደግሞ በደንብ ተጽናንቷል…. በፈረንጆች አቆጣጠር በ2006ዓ.ም በደንብ ደግሶ ቤተሰቦቹን ብቻ እንድናጅበው አድርጎ…..አስደስቶን ነበር ወደ ሃገሩ የተመለሰው አሉን። እኛም ታደሰ ኢትዮጵያ በመጣ ወቅት እነዚያ የሟች ቤተሰቦች እንዴት አልፈለጉትም ብለን የታደሰን አጎት ጠይቀነው ነበር? የታደሰ አጎትም…. ታደሰ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ..... አንድ የተባረከ ልጅ ቴዎድሮስ ከሚባል ጋር በኬንያ አድርገው  ነበር የመጡት...... ቴዎድሮስም ነገሮችን ሁሉ ይከታተልለት ነበር….ሁልጊዜ ከሱ ጋር አብረው ነው የሚወጡትም የሚገቡትም....... ደግሞም በድብቅ ስለሆነ የመጣው...... ከቤተሰብ በቀር ማንንም አያውቅም…. ሰርጉንም ቢሆን እኮ እኛ ቤተሰቦቹ ብቻ ነን የተጋበዝነው አሉን....... እኛም ታሪኩ እውነት መሆኑን አረጋገጥን።  

ታደሰ፤  አዲስ አበባ በነበረበት ወቅት…. ምን አይነት ስራ ይሰራ እንደነበር…..ብዙ ታሪኮች አሉ፤ ነገር ግን አሜሪካ ላይ ከሚሰራቸው ስራዎቹ ጋር አብረን ጣልቃ እያስገባን እናስነብባችኋለን ተከታተሉን።

ታደሰ ወደ አሜሪካ ከመጣ በኋላ ያለውን ታሪክ በሰፊው እዘረዝረዋለሁ ይጠብቁን…………

Saturday, 15 June 2013

ታደሰ የኋላእሸት አለምነህ ማነው?

የቀበሮ ባህታዊ? ዝርዝሩን እነሆ.....

*    ከአሜሪካ ወደ ሐገር ቤት በምን ምክንያት ተመለሰ፤ ስንት ጊዜስ ቆየ?
*    ባለቤቱንስ በሰላም አግኝቷት ይሆን?
*    አዲስ አበባ በሚኖርበት ወቅት ምን ይሰራ ነበር?
*   ስለ ታደስ የኋላእሸት አለምነህ የሕይወት ታሪክ ጉዳይ.....የታደሰ ታላቅ እህት ጸሐይ እና ታናሽ ወንድም ይርጋለም ያደረግነውን ቃለ መጠይቅ እነሆ.......

ክፍል ሦስት 

ታደሰ የኋላእሸት ባለቤቱን እሱ በፈለገው መልኩ ሆኖ ስላገኛት፤ ታማኝነቷን ጠብቃ በመገኘቷ ምክንያት….. ደስታው ከመጠን በላይ እንደሆነ ጸሐይ አብራርታልናለች።  እሱ ካነጸው ከተንጣለለ ቤት ውስጥ አብረው ለ7 ወር ከተቀመጠ በኋላ፤ ታደሰ በኖረባት በዚያች ሰባት ወር ውስጥ ትልቅ ቁም ነገር ሰርቶ መጣ…እሱም ለሌላኛው ወንድሙ እዛው ደብረታቦር ከተማ ……አንድ ቤት ገዝቶ…. ቁልፉን ካስረከበ በኋላ፤ የሥራ ጉዳይ…..የኑሮ ጉዳይ ነውና…..ባለቤቱን ለቤተሰቦቹ፤ ቤተሰቦቹን ደግሞ ለባለቤቱ አደራ ሰጥቶ…..ባለቤቱ አስማረችም እንዳትከፋበት….. ከማናቸውም በላይ መጀመሪያ ከገዛው ቤት ከወላጆቹ ጋር አብሮ ካስቀመጠ በኋላ… ባለቤቱ አስማረች በቤቱ ማዘዝ እንደምትችል ውል ሰጥቶ…… ጉዞውን ወደ ሲያትል እንዳደረገ በታላቅ እህቱ በጸሐይ አንደበት ተነግሮናል።   እኛም ልጅ ወልደዋል ወይ ብለን ጠይቀናት ነበር……. ምክንያቱም የ6 ዓመት ልጅ ከቤታቸው አለና።  እሱን እንኳ የማውቀው ነገር የለም አለችን…..ሕጻኑን እያየነው ለማናገር ያልጣርነው ጥረት አልነበረም….. ነገር ግን አልተሳካልንም።  ስለዚህ ሕጻን ልጅ ጉዳይ ጎረቤቶችን ጠይቀን ነበር….. የማን ልጅ እንደሆነ አናውቅም…… ልጁ የ 3 አመት ልጅ ሆኖ ነው ካስማረች ጋር የመጣው አሉን። ደጋግመን ጸሐይን እየጋበዝን ስለ ታደሰ ማንነት እና ልጁ የማን እንደሆነ እንድታስረዳን ጠየቅናት….. እርሷም  የተወሰነ ጊዜ ካንገራገረች በኋላ….. እውነት ምንጊዜም መውጣቱ አይቀር አለችና…….. አስማረችን በእርግዝናዋ ወቅት ባለቤቷ ታደሰ የኋላእሸትን ቦሌ ድረስ ሸኝታ…… በእንባ ተራጭታ…. ከተመለሰች በኋላ…….. መቀመጫዋን ባህርዳር እንድታደርግ እና ሆስፒታል እየተመላለሰች በቂ ህክምና እየተደረገላት እስክትወልድ ድረስ…… እዛው ባህርዳር እንድትቀመጥ በባለቤቷ በታደሰ ትእዛዝ አማካኝነት ተላለፈ።  እንደ ታላቅ እህቱ ጸሐይ አገላለጽ፤ አሜሪካ ከሄደም በኋላ በሳምንት ሁለት ጊዜ እየደወለ ስለ ጤንነቷ ይጠይቅ ነበር፤ እንዴ የተጎዳ ሰው መቼም ሁለተኛ ይጎዳ አይባልምና….አስማረችን ሁላችን ቤተሰቦች በሙሉ እየተመላለስን አንጠይቃት ነበር፤ ታናሽ ወንድሙ ይርጋለምም…. ባህርዳር ከሷ ጋር ሆኖ አብሮ እስክትወልድ ድረስ ተንከባክቦ እዚህ አድርሶለታል፤ እና ይሄ ባይታደል ነው እንጂ ሁለተኛ ልጁ ነበር….ግን ያለፈው አልፏል….አሁን ጥሩ ሁኔታ ነው ያሉት።  ታደሰም ባለቤቱ በሰላም መገላገሏን ስናበስረው….. ደስታው ከመጠን በላይ በመሆኑ ምክንያት…. አሜሪካ ያለው ሌላ ወንድማችን ከፍቅረ ድንግል የኋላእሸት ጋር አብረው ደጎስ ያለ ገንዘብ ተልኮ…3 በሬ ታርዶ…በደንብ ተደግሶ…. ነበር የልጁ ክርስትና የተከበረለት። የልጁ ስም ማን ይባላል ብለን ጠየቅናት….አባቱ (ታደሰ) ያወጣለት ስም ታደለ ታደሰ የኋላእሸት ይባላል አለችን።  የታደሰ እናት ለልጁ ያወጣችለት ስም “ሐዘኑን አሁን ገና ረሳ ስትል ደስታው ታደሰ የኋላእሸት ነው” አለችን።  ትምህርት ቤት ከገባ በየትኛው ስም ነው የሚመዘገብ? ብለን ጠይቀናትም ነበር….እንደ ጸሐይ አገላለጽ፤ ደስታው ይመስለኛል….ምክንያቱም ሁላችንም የወደድነው ደስታው የሚለውን ስም ነው…… ነገር ግን አባቱ ታደለ ተብሎ እንዲጠራ ስላዘዘ…… እስካሁን በሁለቱም ስም ይጠራል አለችን።  እንደ ጸሐይ አገላለጽ፤ ወንድሜ፤ በጣም ያሳዝነኛል….ለምን ተመላልሶ እንደማይመጣ ግልጽ አልሆነልኝም….እንዳንዴ ስለ እኔ ማንንም ቢጠይቃችሁ አትናገሩ ይላል….አንዳንዴ ደግሞ ወያኔ መምጣቴን ካወቀ ሊገድለኝ ስለሚችል ለማንንም ሰው የኔን ማንነት አትናገሩ፤ አንዱን ልጄንም ታስገድሉብኛላችሁ ይለናል….የሚገርማችሁ እሱ እኮ ማንንም አልገደለም…..ለምንድን ነው ወደዚህ የማይመጣው….እባካችሁን ንገሩት አይገድሉትም…..ባለቤቱም ብቻዋን እየተሰቃየች ነው ያለችው….አንድ ሰው ካገባ በኋላ አብሮ መኖር ተገቢ ነው…….. ግን እሱ ለምንድን ነው የሚፈራው? አሳምኑት እና በፈለገው ጊዜ እንዲመጣ ገፋፉት…..እኛም ቤተሰቦቹ ናፍቀነዋል….ማየትም እንፈልጋለን……ገንዘቡ ብቻ ምን ያደርግልናል ብላ ከእንባ ጋር ነገረችን…..እኛም የጠየቀችንን ጥያቄዎች ለታደሰ በጥንቃቄ እንደምናቀርብ እና ታደሰንም ገፋፍተን ለብዙ ጊዜያት የናፈቃቸውን ባለቤቱንና አንድ ልጁን ወደ አሜሪካ አምጥቶ የሚቀላቀልበትን ሁኔታ እንደምናመቻች ቃል ገባንላት......(ወደ አሜሪካ እንደተመለስንም አነጋግረነው ነበር ይህን ጉዳይ በሌላ ጽሑፍ እመለስበታለሁ)

በተጨማሪም፤ የታደሰ ታናሽ ወንድም ይርጋለምን ታደሰ አዲስ አበባ በነበረበት ወቅት ምን ያደርግ እንደነበር አነጋግረነው ነበር……እንደ ይርጋለም አገላለጽ፤ ታደሰ አዲስ አበባ በነበረበት ወቅት…. አዲስ ፍቅር፤ አዲስ አፍላ….ይዞት ስለነበር….. እኔን ከነመፈጠሬ የረሳኝ ጊዜ ነው…… ምክንያቱም አስማረችን የተዋወቀበት እና በፍቅር የከነፈበት ወቅት በመሆኑ ማንንም አያስታውስም።  በተጨማሪም ከሚያገለግልበት ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከአብዛኛው ምዕመን ጋር ይጣላል፤ ሰላምታም አይሰጣጡም…… ከካህናቱ ጋር ሰላም የለውም….በቅናት መንፈስ ይጣላሉ፤ ምን እንደሚያጣላቸው ግን ግራ ይገባኛል። በአጠቃላይ እርሱ ከአብዛኛው ካህናት ጋር ተጣልቷል ማለት ይቻላል….ከህዝቡም ጋር ቢሆን እንደዚሁ። አንድ ወቅት…. አባታችን እህል አስፈጭተህ ይዘህለት ወደ አዲስ አበባ ከታደሰ ዘንድ ሂድ ብሎ አዞኝ ነበር…እኔም እንደታዘዝኩት አድርጌ….. ትኬቴን ቆርጬ….. ወደ አዲስ አበባ ጉዞየን አቀናሁ…እንደደረስኩ እለቱ ቅዳሜ ነበርና ታደሰን አገኘሁት…..ታደሰም በደስታ አልተቀበለኝም…..ምክንያቱም …..እኔ ከቤተ ክርስቲያን ያሉት ካህናት ቤቱን አመላክተውኝ ስደርስ….እሱ እህቴ ናት ብሎ አስማረችን ለካህናቱ ሁሉ አስተዋዉቆ ነበር….ቅድስት ስላሴ የሚያገለግሉት ካህናት…. እኔን አስማረች የምትባል እህት አለቻችሁ? ብለው ጠይቀውኝ ነበር…..እኔም የለንም….አስማረች የሚባል ስም ጭራሽ ከቤተሰቦቻችን ውስጥ ማንም አይገኝም አልኳቸው…… እነሱም የአሽሙር ሳቅ ስቁብኝና……ማነው ስምህ አሉኝ….እኔም ይርጋለም የኋላእሸት እንደምባል ነገርኳቸው…. እነሱም ሊቀ ዲያቆናችን ባለጌ ነው….. እቃውን (መሽኝያውን) መሸከፍ ያቃተው ነውረኛ…..እግዚአብሔርን የሚዳፈር…..ሴት ልጅ እህቴ ናት እያለ….. እየደለለ የሚባልግ ባለጌ….አግብቶ በነጻነት ቢያደርግ አይሻለውም ነበር?……ቤተ ክህነት እንከሰዋለን….ከሚዋረድ ከዚህ ቢጠፋ ይሻለዋል…… ንገረው ብለውኝ ሄዱ።  እኔም በነገሩ ግራ ገብቶኝ ነበር….ስለማን እንደሚያወሩም አላወኩም ነበር……ታዲያ ያኔ ቤት ገብቼ ወንድም ጋሼን (ታደሰን) ካገኘሁት በኋላ…..ያመጣሁትን እህል አስረክቤ….. አልቦኝ ስለነበር ፊቴን እና እግሬን ታጥቤ የተወሰነ ሰዓት ካረፍኩ በኋላ…..ታደሰ ስለቤተሰቦቻችን ደህንነት ጠየቀኝ….በዚሁ አጋጣሚ ስለቤተሰቦቻችን ደህንነት ከተነጋገርን በኋላ…እሱም ሃዘኑን ረስቶ ደስተኛ መሆኑን ካረጋገጥኩ በኋላ….እኔም ደስ ብሎኛል ስለተጽናናህ አልኩት…..ምን ይደረግ ብለህ ነው እግዚአብሄር ሰጠ…እግዚአብሄር ነሳ አለኝ። እኔም ቀጠልኩና አስማረች የምትባል እህት አለህ ብለው ጠየቁኝ አልኩት….ታደሰ ግን ከመቀመጫው እንዴት እንደተነሳ አስደነገጠኝ…ብቻ ፍንጥር ብሎ ተነሳና ምን አልካቸው አለኝ….እኔም…በድርጊቱ ደንግጬ ወንድም ጋሸ ተረጋጋ ….እኔ ያልኳቸው…በፍጹም አስማረች የምትባል ጭራሽ በዘራችን የሚጠራ ስም የለም ብዬ ንግግሬን ሳልጨርስ አጎዛ….ዝተት….አንኮላ….ማንነቱን ለማታውቀው ሰው ዝምብለህ ትለፈልፋለህ እያለ ሲሳደብ እና ሲማታ አስማረች እንዳጋጣሚ ከተፍ አለች። (ከጋብቻ በፊት ሁለተኛ ባለቤቱን አሳምሮ ይደስቃት ነበር ማለት ነው አልኩ በልቤ……… አለበለዚያ እንደዚህ አያስደነግጠውም…….ምናልባት ያ ይሆን ወደ ኬንያ ያሰደደው? ወይስ ሌላም ጉዳይ ጭምር አልኩ በውስጤ እያንሰላሰልኩ……..እስኪ የጀመረውን ታሪክ ይጨርስልንና እነዚህን ጥያቄዎች ይመልስልናል)።  ከዚያስ አልነው ይርጋለምም ቀጠለና እንዲህ አለ……
ይቀጥላል……………
ታደሰ ወደ ኬንያ የሄደበት ምክንያት ምን ይሆን በሚቀጥለው ይጠብቁን




Wednesday, 12 June 2013

ታደሰ የኋላሸት አለምነህ ማን ነው?

የአሁኑ የቀበሮ ባህታዊ አባ መላከ ብርሃናት ገብረሥላሴ የኋላሸት አለምነህ....... ይሄ ዘለፋ አይደለም እውነተኛ ታሪክ ነው.....መልካም ንባብ!!!

ክፍል ሁለት
ታደሰ የኋላሸት አለምነህ አዲስ አበባን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲመለከታት አብረቅርቃ ስለታየችው፤ አልወደዳትም ነበር፤ እኔም በሆዴ አይ…የባላገር ነገር ብዬ ሳላስበው ጮክ ብዬ ተናገርኩ….…ወንድሙን ከልቡ አሳኩት፤ እኔም ደንግጨ ይቅርታዬን ጠየኩ……ጨዋታችንን ቀጠልን…..የታደሰ ታናሽ ወንድም ይርጋለምም ቀጠለና፤ ወንድም ጋሼ (ታደሰን) አዲስ አበባ ከሄደ በሶስተኛ ወሩ….. ወባ በሽታው ተነስቶበት ከሞት ስለተረፈ፤ ተሎ ፈጥኖ በመወሰን ጉዞውን ወደ ደብረታቦር ለመመለስ አቅዶ እንደነበርና፤ ያቀደውን እቅድ አባታችን ስላልተቀበለው፤ በአባታችን ምክርና ተግሳጽ ምክንያት እዛው አዲስ አበባ እየታከመ እንዲቆይ ሆነ።  
ታደሰ፤ በባለቤቱና ሳይወለድ ሕይወቱ በተቀጨው ልጁ ሞት ተጎድቶ ስለነበር፤ ሐዘኑም አዲስ አበባ ተከትሎት ስለመጣ፤ አጎታችንም የሱን ትካዜና ሐዘን ማስቆም ስለነበረበት….… ምክር ቢለግሰውም አልሰማ ስላለ…....ሁሉን ነገር እንዲረሳ በሚል ሃሳብ በፍጥነት የማታ ትምህርት ቤት አስገባው። ታደሰ በዲቁናው እያገለገለ ከሚያገኛትም ደሞዝ ለተወሰነ ወራት፤ ወለም ዘለም ሳይል ወላጆቹን ሲረዳ ቆይቶ፤ ሳያስበው ትምህርት ቤት አስማረች ዘለዓለም ከምትባል ወጣት ጋር በመተዋወቁ ምክንያት ለመጀመሪያ ጊዜ ድብን ያለ ፍቅር ይዞት ቁጭ አለ።  ወይ የባላገር ፍቅር አልኩ በልቤ…. ከዛም ይገርማል አልኩት ለይርጋለም….. እሱም በጣም እንጂ….….ወንድም ጋሼ (ታደሰን) ለመጀመሪያ ጊዜ ደስተኛ ሆኖ ስላየነው፤ ሁላችንም ቤተሰቦቹ በሙሉ ደስተኞች ነበርን።  አስማረችም ባህሪዋ መልካም ስለነበር፤ ወንድማችንን በደንብ አድርጋ ትንከባከበው ነበር፤ ምግብ እየሰራች ከቤቷ ትመግበው ጀመር….እሱም ለስድስት ወራት ያህል በተከታታይ ማክሰኞ…ማክሰኞ…. ሐዘኑን እንዲረሳ…. እየተባለ… ወደ ናዝሬት ከሌላኛው አጎታችን ከሚኖርበት ስፍራ በመሄድ፤ ለመዝናናት ትወስደው እንደነበርም ገልጾልናል። ከአስማረች ጋር ከተዋወቀበት ዕለት ጀምሮ፤ ለዘመዶቹ ያለው አትኩሮት ቀነሰ፤ ትንሽ ቆይቶም ወላጆቹን መርዳት አቆመ…….ጭራሹኑ ወላጆቻችን ለእሱ (ለታደሰ) ብቻውን እኮ ነው፤ ማን አለለት እየተባለ….. እህል ይላክለት ጀመር። እንደ ታናሽ ወንድሙ ይርጋለም አገላለጽ፤ ስለ ታደሰ ሁኔታ….. በእርግጥ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ነበር የተረዳሁለት….. ምክንያቱም የመጀመሪያ ፍቅር ከባድ ነው አለን። ታደሰ በዲቁና ሥራ እያገለገለ የሚከፈለውን ደሞዝ ምን ያደርገዋል? ብለን ጠየቅነው…… የታደሰ ታናሽ ወንድም ይርጋለም እንዲህ ሲል መለሰልን…..አዲስ አበባ ብዙ መዝናኛ አለ፤ ምንም የሚከፈለው ገንዘብ ትንሽ ቢሆንም………. ሴት ልጅ ከጓደኛዋ ጋር መዝናናትን ትወዳለች….የከተማ ልጅ እኮ ናት… ወዳጄ አለን…..እኛም እርስ በርስ ተያይተን ተሳሳቅን… ይርጋለምም ጨዋታውን ቀጠለ፤ እንዲህ ሲል……ስለዚህ ታደሰም ሐዘኑን በአስማረች ምክንያት ስለረሳልን ደስታችን ወሰን አልነበረውም። 
አንድ ነገር ግን የከፋን ነገር ነበር…ታደሰ ወደ ኬንያ ሊሄድ በተነሳበት ወቅት፤ አስማረች ጋር የቀለበት ስነ ስርዓት አድርጎ ነበር የሄደው፤ ነገር ግን እኛን ሳይጠራን….ሳይጋብዘን….ቤተሰቦቹ አልል ብለን…ዘፍነን ሳንድረው….እንዴት በጓደኞቹ በአገር ደብተራ ታጅቦ…በድብቅ ከአንዱ ጓደኛው ቤት ደግሶ… ቀለበት አድርጎ ይሄዳል……እኛን የገረመን ወላጆቹን እና አጎታችንን (ለዚህ ያበቃውን)፤ቤተሰቦቹን ከቀለበቱ ሥነ ሥርዓት ሳይጋብዝ በመቅረቱ፤ እጅጉን አዝነንበት እንኖር ነበር….ከጓደኛ ይልቅ ቤተሰብ ይበልጥ ነበር…. ነገር ግን ይሄን ያደረገበትን ምክንያት እስካሁን ድረስ ለእኔ እንቆቅልሽ ነው። እንደኔ…. እንደኔ…ይኼ ለእኛ ለቤተሰቦቹ ትልቅ ውርደት ነው፤ ምክንያቱም….. እኛ እሱን ለማስደሰት ደፋ ቀና እንላለን……እሱ በዚህ ክዶን ሄደ።  በዚህ ጉዳይ ተቀይመነው ነበር የምንኖር….. ነገር ግን በ2006 ዓ.ም ከ13 አመታት በኋላ ከአማሪካን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ...... በደንብ ደግሶ...... በእናቲቱ ማርያም ቤተ ክርስቲያን (ደብረታቦር).....  እኛን ቤተሰቦቹን ብቻ እንድናጅበው አድርጎ.......በቁርባን ጋብቻውን  አጽንቶ፤ እኛንም ስላስደሰተን ይቅር ብለናል አለ። (እኔም በውስጤ ከራሴ ጋር እየተነጋገርኩ በመገረም፤ ሁለተኛ ትዳር ይሉሃል ይሄ ነው፤  አይይይ... የታደሰ ክህነት ከፈረሰ ለካ ቆይቷል አልኩ..... ነገር ግን ድርጊቱ እስከ አሁን ድረስ ይገርመኛል)
ከእኔ ጋር አብሮኝ የሄደ አንዱ ጓደኛዬ የታደሰ ታላቅ እህቱን ጸሐይን እንዲህ ሲል ጠየቃት….አንችስ….. ከቀለበቱ ስነ ስርዓት ተጋብዘሻል ወይ? የታደሰ ታላቅ እህት ጸሐይም በቁጣ መንፈስ እንዲህ ስትል መለሰችለት….ወይ መጋበዝ……እሱ በድብቅ አድርጎት ነው እኮ ወደ ኬንያ የሄደው….በዚህ ምክንያት ወላጆቻችን በጣም ያዝኑበት ነበር…”ልቡ የማይገኝ፤ እሾህ፤ ይለው ነበር አባቴ”…. ምክንያቱም እሱን ለዚህ ያበቃው አባቴ ነበር። ቢሆንም…በቤተክርስቲያን ሰዎች እና በካህናቱ ላይ ከተንኮለኞች ደብተራ ጋር አብሮ ያደርገው የነበረው ክፋት እና ተንኮል… በሽታ ላይ ጥሎት ብዙ ያንገላታው ነበር።  አስማረችንም እኮ ቀለበት ካደረጉ በኋላ በጓደኞቹ ደብተሮች አስተብትቦ ለ13 አመት እንድትጠብቀው አድርጓል፤ እሷ ግን እጅጉን ታሳዝነኝ ነበር..አትሰራም…አትማርም…. እንዲሁ ብቻ የቤት እመቤት ሆና ቀርታ ነበር። ቢሆንም መጥቶ ጋብቻውን ስላጸናላት ደስ ብሎኛል፤ አሁን ግን ከእኛ ወላጆች ጋር አብራ ትኖራለች። እግዚአብሔር ይመስገን ለዚህ ላበቃቸው፤ በፊት ግን በጣም አዝኜበት ነበር በማለት ትዝታዋን አጫውታናለች።
ይገርምሃል አለች ጸሐይ….ታደሰን ወደዚህ (ኢትዮጵያ) እንዲመጣ እና እንዲያየን ብዙ ጥረት አድርገን ነበር፤ ነገር ግን  የእርሱ መልስ ሁልጊዜ አንድ አይነት ነበር… “ወያኔ ይገለኛል”… ለምን እንደዚህ እንደሚለን ግን አይገባንም ነበር…..አባታችንም ታደሰን ምን አርገሃል ወያኔ የሚገድልህ ብሎ ደጋግሞ ጠይቆት ነበር፤ታደስ ግን ጥያቄውን መልሶለት አያውቅም..... እንዲሁ ብቻ ብዙ አመት ባለቤቱን ትቶ ተቀምጦ ነበር…ቢሆንም አስማረች ለአባቴ እንዲህ አለችው….እኔ እንግዲህ ሌላ ላገባ ነው….. 13 አመት ጠብቄአለሁ….. ከእንግዲህ ወዲህ ዘር መተካት አለብኝ፤ እድሜዬ ከፍ እያለ ነው.....እሱ ዘንድሮ የማይመጣ ከሆነ… ሌላ አገባለሁ በማለቷ ምክንያት… የታደሰ እናት በፍጥነት ለታደሰ አሜሪካ ድረስ በመደወል….. እንግዲህ እኔ እንደምታውቀው መንኩሻለሁ…አርጅቻለሁ….በጣም አሞኛል…..ከመሞቴ በፊት ፊትህን ልዬው፤ ልባርክህ እና ልሙት ብላ ለታደሰ ትነግራለች……ታደሰም የእናታችንን ቃል ሰምቶ፤ በፍጥነት እዛው እናንተው አካባቢ የሚኖር (ሲያትል) ቴዎድሮስ ከሚባል ልጅ ጋር  በኬንያ አድርገው ደብረታቦር መጡ፤ ያን ጊዜ አስማረች ባለቤቷ ይመጣል ብላ ባላሰበችበት ሰዓት በአካል ስላገኘችው፤ ደስታዋ ከመጠን በላይ ስለነበር፤ ራሷን ስታ ነበር… አስማረችም እንደነቃች ከባሏ ከታደሰ ጋር ያላትን ናፍቆት እንድትወጣ ከእርሱ ጋር ተዋት….. ከዚያስ............................................................................


ከታደሰ የኋላእሸት አለምነህ ታላቅ እህት ጸሐይ ጋር የነበረንን ቆይታ እንመለስበታለን፤ በታደሰ ሕይወት ዙሪያ ከታናሽ ወንድሙ ከይርጋለምም ጋር የነበረንን ቃለ መጠይቅ ማለትም ታደሰ አዲስ አበባ በነበረበት ወቅት ምን እንደሰራ……... ወደ ኬንያ ለመሄድ ያነሳሳው ምክንያት ምን እንደነበር………ወደ አሜሪካ በምን ምክንያት ሊመጣ እንዴት እንደቻለ በሚቀጥለው ክፍል ይጠብቁን………

Monday, 10 June 2013

ለምድ የለበሰ አስመሳይ የተኩላ ባህታዊ፤ ታደሰ የኋላሸት አለምነህ ማን ነው?

ታደሰ የኋላእሸት አለምነህ የአሁኑ መላከ ብርሃናት ገብረስላሴ የኋላሸት አለምነህ ማን ነው?
ይሕ መልእክት ዘለፋ አይደለም...እውነታነት ያለው ታሪክ ነው።
ክፍል አንድ

.
እርግጥ ነው አሁን ታደሰ የ56 አመት ሰው ነው። መቼም ወጣት ለመምሰል የማያደርገው ጥረት የለም፤ ልክ እንደ ወጣት ሴት፤ እዩኝ…. እዩኝ….. እንደምትል ኮረዳ፤ ያሳደገውን ጺሙን ጥቁር ቀለም እየቀባ ወጣት ሲመስል፤ አንዳንዴ ደግሞ ይሰለቸዋል መሰል ነጭ ጢሙ ዥርግግ ብሎ ሲታይ…. ብቻ ያሳፍራል…. የጺሙ ሁኔታ ዚብራ ይመስላል።  ወደ ታሪኩ ልውሰዳችሁ።
ከዚህ ፎቶ ግራፍ ላይ ደግሞ፤ አሜሪካ የዛሬ 2 አመት በዚሁ ቅዱስ ገብር ኤል ሲያትል ደብር ላይ አመንኩሱኝ አለም በቅቶኛል በማለት የምንኩስና ማዕረግ ከተቀበለ በኋላ.... መነኩሴ መስሎ ሲቀድስ ፤ጅብ በማያውቁት ሃገር ሄዶ ቆርበት አንጥፉልኝ ይላል አሉ...ወይ ማጭበርበር፤ ነገር ግን ከአንድ ሴት በላይ የሄደ ሰው ካህን ሆኖ መቀደስ ይችላልመልሱን  እናንተ እተወዋለሁ...ታሪኩን ተከታተሉ...

ታደሰ  የኋላእሸት አለምነህ ጥር 14 ቀን 1949 ዓ.ም በደብረታቦር አውራጃ  ተወለደ። እርሱም ለቤተሰቡ የ3ተኛ ልጅ ነው። ሁለት ታላላቅ እህቶች አሉት።  4 ወንድሞችም አሉት።  ከወራቶች በፊት ኢትዮጵያ ቤተሰቦቼን ለመጠየቅ ከሁለት ጓደኞቼ ጋር ሄጄ በነበርኩበት ወቅት፤ ለአንድ ዓላማ ጉዳይ ደብረታቦር ሄጄ ነበር፤ የታደሰን ቤተሰቦች ደግሞ በዚሁ አጋጣሚ ተዋወቅን፤ ከወንድሞቹ አንዱን ይርጋለም የኋላእሸት አለምነህን ስለ ታደሰ ታሪክ አነጋግረነውም ነበር።  እንደ ታደሰ ታናሽ ወንድም ይርጋለም አገላለጽ፤ ታደሰ ከቤተሰባችን ከወንዶች መካከል በእድሜ ታላቁ እሱ ነው፤ ነገር ግን ወላጆቹን በጣም ያስቸግር ስለነበር፤ አባታችን…. ታደሰን ይሄ ልጅ ገና ከአሁኑ ነገረኛና ቂመኛ ከሆነ ሲያድግ ማንም አይችለውም በማለቱ በ7 አመቱ አያታችን ያሳድገው ዘንድ ተሰጠ።  ከዚያም ከአያቶቹ ጋር መኖር በጀመረበት ወቅት፤ ከጎረቤት ልጆችጋር እየተደባደበ፤ እየተሰዳደበ፤ ድንጋይ እየተወራወረ ሲያስቸግራቸው፤ አያታችንም ቢገርፉትም ባህርይው አስቸጋሪ ሆኖ ስላገኙት፤ ድንገት ይሻሻል ይሆናል ብለው በማሰባቸው ምክንያት፤ በ16 ዓመቱ ቤተ ክርስቲያን ግብረገብ እንዲማር ተደረገ።  ይበልጡኑን ክፋትንና ተንኮልን ጨምሮበት ከቆሎ ተማሪዎች ጋር እየተደባደበ ሲያስቸግር፤ እስኪ ልዳረው....... ያን ጊዜ ትንሽ ሰከን ይላል፤ ልጅነትም ይቀራል፤ በማለት በ18 አመቱ አንዲት ትንሽዬ የ14 አመት  ትዕግስት ፈረደ ከምትባል ልጅ ጋር ወላጆቹ እና አያቱ አጋቡት።  የታደሰ ወላጆቹ ገበሬዎች ነበሩና፤ በወላጆቹ እየተረዳ እስከ 21 አመቱ ድረስ ከልጅቷ ጋር አብረው 3 አመት አንድ ቤት ውስጥ ይኖሩ ነበር ትዳራቸውም ደርቶ እንደነበርና አንዳንዴ ይደበድባት እንደነበርም ይርጋለም አጫውቶናል። በተጨማሪም እንደ ይርጋለም አገላለጽ፤ የታደሰ ባለቤት በልጅነቷ አርግዛ በወሊድ ምክንያት ልጇም እሷም አብረው እንዳረፉ፤ ታደሰ ደግሞ በተፈጠረው ሁኔታ እንደተጎዳ እና ከመጠን በላይ እንዳዘነ ነግሮናል።  በዛን ወቅት ታደሰ እና ባለቤቱ የሚኖሩትም በገጠር ስለነበር፤ ባለቤቱን ሆስፒታል ለመውሰድ ጥረት ቢያደርግም፤ በጊዜው  ሕክምና ባለማግኘቷ ምክንያት ሕይወቷ በቀላሉ ሊያልፍ ቻለ።  ታደሰ የሚችለውን ያህል ጥረት አድርጎ ሳይሳካለት በመቅረቱ፤ ባለቤቱንና ሳይወለድ የሞተውን ልጁን ሳያይ፤ ሁለቱም በመሞታቸው ምክንያት ታላቅ ሃዘን ላይ ነበር። 

በአንድ ጊዜ ሁለት ሰው ማጣት ከባድ ቢሆንም፤ ታደሰ በሃዘን ምክንያት ተጎድቶ ስለነበር፤ ወላጆቹም የሱን ትካዜና ሃዘን ማየት ስላልፈለጉ፤ ከቦታው እንዲርቅ በማለት አዲስ አበባ ካለው ወንድማቸው (ለታደሰ አጎት) ዘንድ እንዲቆይ እና ዘመናዊ ትምህርትም እንዲማር በሚል ሃሳብ ወደ አዲስ አበባ እንዲሄድ ተደረገ።  ከተወሰነ ወራት በኋላ፤ አጎትዬው ታደሰን ከቤተክህነት ካሉት አባቶች ዘንድ አስተዋውቆ ቅድስት ስላሴ ካቴድራል አዲስ አበባ፤ በዲቁና እንዲቀጠር አደረጉ።   የዘመናዊ ትምህርት ቤትም በአጎቱ አማካኝነት ተመዝግቦ ማታ ማታ መማር ጀመረ፤  ከዚያስ..........

በታደሰ የኋላእሸት ሕይወት ዙሪያ ከይርጋለም እና ጸሐይ ጋር ያደረግነውን ቃለ መጠይቅ እና ታደሰ የኋላእሸት በአዲስ አበባ የነበረው ቆይታ እንዴት እንደነበር እመለስበታለሁ ተከታተሉን? ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብቶ በሚማርበት ወቅትስ ምን ያደርግ ነበር? ይህን በሚቀጥለው ጽሑፌ እመለስበታለሁ ይጠብቁን….




የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ችግር፤ ሲያትል

ቀን ግንቦት 11፣ 2005 ዓ.ም
May 19, 2013 G.C
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
“እግዚአብሔርን ያይደለ እናንተን ልንሰማ በእግዚአብሔር ፊት ይገባልን? እስኪ እናንተ እራሳችሁ ፍረዱ። እኛ ያየነውን እና የሰማነውን ነገር ከመናገር ዝም እንል ዘንድ አንችልም” ሐዋ 4፤19
ለብጹዕ አቡነ ሉቃስ የሲያትል መካነ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሊቀጳጳስ እና ለመካነ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን
አስቀድመን የ እግዚአብሔር ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን እያልን ሁላችሁም እንደምታውቁት እና በተደጋጋሚ እንደገለጽነው ደጉ አባታችን ለቀ ጳጳስ አቡነ ዜና ማርቆስ ካረፉ በኋላ የቤተክርስቲያናችን አስተዳደር ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበላሸ እና መፍትሔ እያጣ መምጣቱን በዚህ መልኩ ለምዕመናን ለመግለጽ እንወዳለን።
በነሐሴ 21፣ 2003 ዓ.ም ደጉ አባታችን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ዜና ማርቆስ ያሰመጡልን መምህራችን አባ ገብረሥላሴ ጥበቡ ያለአግባብና በግል ጥላቻ ከቤተክርስቲያናችን መወገዳቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ያለውን የቤተክርስቲያናችንን ችግር መፍትሔ እንዲያገኝ ተሰባስበን የጠየቅነውን ጥያቄ እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ያለምንም መፍትሔ ሁለት አመት ሊያስቆጥር ጥቂት ወራት ቀርተውታል።  ይህንን ደብዳቤ ለመጻፍ የተነሳንበት ዋና አላማ ባለፈው በመስከረም 23፣ 2005 ዓ.ም ምዕመናኑ ተሰባስቦ የመጨረሻ መፍትሔ እና ሙከራ እንዲያደርጉ ከዚህ በፊት የመረጥናቸውን 13 ሽማግሌዎች ወደ ብጹዕ አቡነ ሉቃስ ፊት ቀርበው እንዲነጋገሩ ተልከው ነበር በዚህም መሰረት ሽማግሌዎቹ ከብጹዕ አቡነ ሉቃስ ሊቀ ጳጳስ ጋር ተገናኝተው ጉዳዩን እሳቸው በሾሟቸው ሰዎች አማካኝነት እንደሚወያዩና መፍትሔ እንደሚሰጡ ባዘዙት መሰረት በህዝብ የተመረጡት ሽማግሌዎች የሊቀጳጳሱን ቃል አክብረው እሳቸው ካስመረጧቸው ሰዎች ጋር በተደጋጋሚ ተነጋግረዋል። በውጤቱም ምዕመኑ በቤተክርስቲያኑ ጉዳይ ምንም እንደማይመለከተው እና የነሱ ስራ የተጣላ ሰው ካለ ማስታረቅ ብቻ እንደሆነ አሳውቀው ሽማግሌዎቻችንን አሰናብተዋል።
እኛም ይህንን ውሳኔያቸውን በሚመለከት እንደማንስማማ ምዕመኑ የቤተክርስቲያኑ ባለቤት እንደሆነ እና ማንኛውም ጉዳይ ስርዓቱን ጠብቆ ማወቅ መረዳት እንዳለበት ለዚህም ሊቀጳጳሱ አቡነ ሉቃስ ሐላፊነት እንዳለባቸው የሚያስገነዝብ ሁለት ገጽ ደብዳቤ መጋቢት 24፣ 2005 አስገብተናል።  አያይዘንም ምዕመኑ ሰብስበው መፍትሔ እንዲሰጡ ጠይቀናል። ይሁን እንጂ ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ሉቃስ እስከዚህ በፊቱ የምዕመናኑን ጥያቄ ችላ በማለት በህዝቡ ስም ያለ ምዕመኑ እውቅና የተለያዩ ስራዎችን እያደረጉ ይገኛሉ።  ይባስ ብለው ባለፈው ሳምንት ያለ ምዕመናኑ እውቅና እና ተሳትፎ ቦርድ ኦፍ ትረስቲ አቋቋሙ።  ከዛም በፊት እ ኤ አ በጃንዋሪ 20፣ 2013 ምዕመናኑ ባልተሰባሰበበት እና በማያውቀው ጉዳይ ሁለት ሶስተኛው አባል ተሰባስቦ ፈርመዋል ተብሎ ምዕመናኑ የማያውቀው መተዳደሪያ ደንብ መሻሻያ እንደተደረገበት የሚያሳውቅ ወረቀት በጃንዋሪ 22፣ 2013 ኦሎምፒያ ተመዝግቦ ይገኛል። (ይህንን የመሳሰሉ ምዕመናኑ ሳያውቀው በስማቸው ተፈርሞ ኦሎምፒያ የገባ ብዙ ዶክመንት በእጃችን ይገኛል። ዛሬ በአውደ ምሕረቱ ተገኝተን ጥያቄያችንን ይመለስልን ከማለታችን በፊት ብዙ መንገድ ተጉዘናል፤ ጥቂቶችም እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል።
·         ደጉ አባታችን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ዜና ማርቆስ ያሰቀመጡልንን የወንጌል መምህር በግል በተፈጠረ ጠብ ከቤተክርስቲያን አገልግሎት ሲይስወግዱ በነሐሴ 21፣ 2003 ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ ካሉት ሁለት ሊቃነ ጳጳሳት እና ሊቀ ካህናት ሽምግልና በመላክ ሠላም እንዲፈጠር ጥረናል።
·         በሊቃነ ጳጳሳቱ የተሞከረው ሰላም ባለመምጣቱ አባታችን አቡነ ሉቃስ ልጆቻቸውን አይንቁም በሚል የሚያስታርቁ ብጹዓን ናቸው ብለን ሰላም እና እርቅ እንዲመጣ በመስከረም 28፣ 2004 ዓ.ም ለእርሳቸው እና ለቤተ ክርስቲያኑ ቦርድ ደብዳቤ አስገብተናል።
·         በጥቅምት 12፣ 2004 ዓ.ም እርሳቸው ከእኛ ጋር ለመነጋገር ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ከቤተ ክርስቲያን ቦርድ አባላት ጋር በመነጋገር ችግሩ አስተዳደራዊ መሆኑን ተገንዝበናል።
·         በጥቅምት 19፣ 2004 ዓ.ም ለእርሳቸው እና ለቦርዱ አባላት አጠቃላይ የምዕመናኑ ብሶት ዘርዝረን መፍትሔ እንዲሰጠን በ4 ገጽ ደብዳቤ ጠይቀናል
·         እ ኤ አ በጥቅምት 22፣ 2010 እርሳቸው ከእኛ ጋር ለመነጋገር ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ቅ/ሲኖዶስ በሊቀ ጳጳስ አቡነ መልከ ጼዴቅ በተጻፈ ደብዳቤ የቤተ ክርስቲያኑ የበላይ ጠባቂ አድርጎ በሾሟቸው መሠረት እኛም የተለያየ ችግር እንዳለብን የሚያስውቅ ደብዳቤ እና ወኪል በሕዳር 3፣ 2004 ዓ.ም ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ ልከናል።  ቅዱስ ሲኖዶሱ መፍትሔ ባለመስጠቱ ባሻገር ወኪላችንን ሊቀ ጳጳሱ አውደ ምሕረቱ ላይ በመሆን ከፍተኛ ሞራልና ልብ የሚነካ እጅግ አሳዛኝ የሆኑ ቃላትን ሰንዝረዋል።
·         ቅዱስ ሲኖዶስ ምንም መፍትሔ ስላልሰጠን እና ችግራችንን ስላልሰሙን በታህሳስ 16፣ 2004 ዓ.ም የደረስንበትን ጉዞ እና አጠቃላይ አካሄዳችንን በአጭሩ ለምዕመናን በበራሪ ወረቀት አሳውቀናል።
·         በየካቲት 18፣ 2004 ዓ.ም ምዕመናኑ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ባለ አዳራሽ በመሰብሰብ የደረስንበትን አሳውቀን 13 አባላት ያሉበት የቤተ ክርስቲያን ታላላቅ ሰዎችን ያካተተ ሽማግሌ ሕዝቡ መርጦ ጉዳዩ በሰላም እንዲፈታ ወደ እርሳቸው ሽምግልና ልከናል፤ ከቦርድ አባላት ጋርም ተነጋግረናል።
·         በቅዱስ ሲኖዶሱ ተስፋ ያልቆረጠው ምዕመን በአመት ሁለት ጊዜ በሚካሄደው መደበኛ ስብሰባ መፍትሔ እንዲሰጠን በተደጋጋሚ ደብዳቤ ልከናል፤
·         በያዝነው አመት መስከረም 23፣ 2005 ዓ፣ም ም ዕመናኑ የወከላቸው ሽማግሌዎች ለመጨረሻ ጊዜ እንዲያናግሩ ልከናል
ይሁን እንጂ ለተጠየቅነው ጥያቄ በአግባቡ መልስ ሳይሰጠን እና ወደ ጎን በመተው በጹዕ አባታችን አቡነ ሉቃስ ሊቀ ጳጳስ ያለ ምዕመኑ እውቅና፤
1.      ቤተ ክርስቲያናችንን ወደ ገዳምነት ቀይረዋል፤ ምንም እንኳን ገዳም በመሆኑ ምንም ተቃውሞ ባይኖረንም፤ ገዳም በመሆኑ ምን እንደምንጠቀም፤ ምን እንደምናገኝ እና እንደምናጣ ካለማወቃችን ባሻገር የምዕመኑ ጥያቄ እንደሆነ ተደርጎ ለቅዱስ ሲኖዶስ መቅረቡና ም ዕመናኑ ተስማምቶበት ያጸደቀው ነው ተብሎ ያለ ምዕመናኑ እውቅና ኦሎምፒያ መዝገብ ቤት መግባቱ አሳዝኖናል፤
2.     እንዱ ጥያቄያችን በቤተ ክርስቲያናችን በሚደረገው የአገልግሎት ምርጫ ምዕመኑ የአባልነት መብቱ ተጠብቆ ይምረጥ ይመረጥ ቢሆንም በተቃራኒው ምዕመናኑ ሳይሳተፍበት የተለያዩ የኮሚቴ ምርጫ የተካሄደ ሲሆን በተለይም ያለፈው ሳምንት የተሾሙት ቦርድ ኦፍ ትረስቲ በጣም የሚያሳዝን ሆኖ እግኝተነዋል፤ በመሆኑም በዛሬው ዕለት በዓውደ ምሕረቱ ቆመን በድጋሚ እስካሁን ጥያቄያችንን መልስ እንዲሰጠው እንጠይቃለን፤ ጥያቄዎቹም ባጭሩ አስቀምጠነዋል።
·         ቤተ ክርስቲያናችን እንደማንኛውም በሰሜን አሜሪካ ሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ ስር እንደሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት በቅዱስ ሲኖዶስ ሕግና ስርዓት ትመራ
·         በቤተ ክርስቲያናችን እንደሚታወቀው የመተዳደሪያ ደንቡ ምዕመኑ ስለለለው መብቱን እና ግዴታውን ስለማያውቅ፤ እንዲያውቅ እና እንዲረዳ፤ መምረጥ ሆነ መመረጥ መብቱ እንዲጠበቅ፤
·         በመተዳደሪያ ደንቡ እንደተጠቀሰው እና እንደሚያዘው የሰበካ ጉባኤ አባላትም ይሁን የቦርድ አባላት ወይም የቦርዶ ኦፍ ትረስቲ አባላት አገልግሎት ዘመን እንዲኖራቸው እና የአገልግሎት ዘመናቸው ሲያልቅ ሌሎች አገልጋዮች በምትካቸው በምልዐተ ጉባኤ እንዲመረጥ፤
·         በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት ቤተ ክርስቲያናችን የኦዲት እና ቁጥጥር ኮሚቴ ተመርጦ አጠቃላይ የሒሳብ እና ንብረት ምርመራ እንዲደረግ፤
·         በምዕመናኑ ስም እና ገንዘብ የተሰሩ ስራዎች በጥቂት ለሰቦች እንዲሰሩ ተደርጎ የሚቀርቡ ስራዎች እንዲወገዱና የህዝብ ባለቤትነት እንዲረጋገጥ እንዲሆን፤ ለዚያ ማሳያ ባለፈው በደጉ አባታችን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ዜና ማርቆስ ስም በተሰራው መታሰቢያ ሕንጻ የተቀመጠው ድንጋይ ላይ ቤተ ክርስቲያኑን ገንብተው በጉልበትም በገንዘብም እዚህ ያደረሱትን ምዕመናን ከኛ ጋር ይሉትም ሆነ በሕይወት የሌሉትን ዘንግቶ የጥቂት ግለሰቦች ስም መቀመጡ ያደባባይ ምስጢር ነው።
·         ሁሉም ምዕመናን እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነታቸው ማግኘት የሚገባቸው አገልግሎት ያለምንም አድሎና መድሎ ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ እንዲደረግ፤ በተቃራኒው አንዱ እንደ ልጅ ሌላው እንደ እንጀራ ልጅ በመታየት ሊባርኩን በያዙት መስቀል አንዱን ሲያሳልሙት አንዱን ሲነሱት፤ ከልጆቹና ከራሱ ጉሮሮ ነጥቆ በሰራው ቤተ ክርስቲያን አንዱ ስለቱን ሲለምን ሌላው ስለቱን አትለምንም ሲባል፤ ለበረከት አገልግሎት ሊሰጥ ተገፍትሮ ውጣ ሲባል፤ ክርስትና ለማስነሳት፤ ፍትሐት ለማስፈታት፤ በተክሊል በስጋ ወደሙ ለመጋባት እና የድጋፍ ደብዳቤ ለማግኘት አግባብ የሌለው የገንዘብ ተመን ከአቅሙ በላይ የተጠየቀ ምዕመን ቤቱ ይቁጠረው።
·         ቤተ ክርስቲያናችን የተደራጀ የሰንበት ትምህርት ቤት ስለለለው አጠቃላይ ወጣቱ፤ ሕጻናቱን እና ሀገር ተረካቢውን ትውልድ የሚያካትት ሰንበት ትምህርት ቤት እንዲቋቋም የሚሉ ሲሆን፤
እነዚህን ጥያቄዎች መጠየቃችን እንደነውር ተቆጥሮና ሌላ ስም ተሰኣጥቶት እስካሁን ድረስ መልስ ሳይሰጠን ቆይተናል፤ በአንጻሩ የዋሁን የቤተ ክርስቲያናችንን ምዕመን በቡድን በመከፋፈል እና የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ይህንን ጥያቄ የሚጠይቁትን ምዕመናንን ፤
1.      አባቶችን ሊያባርሩ ቤተክርስቲያኑን ሊወርሱ የተቋቋሙ ናቸው እያሉ የከሱናል፤
2.     የተወሰኑ ክፍለ ሐገር ሰዎችን በመጥቀስ ከዚህ ቦታ እንደዚህ ያለውን ክፍለ ሐገር ለማስወገድ የተነሱ ናቸው ብለው የሐገራችን ወቅታዊው መንግስት የሚጣእቀምበትን የመከፋፈል መንገድ እየተጠቀሙ ሊከፋፍሉን ይሞክራሉ፤ እኛ ግን በጎሳና በዘር ሳይሆን በአንድ የቤተክርስቲያን ልጅነት እና በኢትዮጵያዊነት እናምናለን።
3.     ቤተ ክርስቲያኑን ለግለሰብ ሊያስረክቡ የተነሱ ናቸው ይሉናል፤ ነገር ግን እነሱ እንደምያስቡት ሳይሆን ከላይ የዘረዘርናቸው ጥያቄዎች እንዲመለሱ የምንፈልግ ምዕመናን መሆኑ ታውቆ ጥያቄያችንን እንዲመልሱ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
እግዚአብሔር አምላካችን ለቤተክርስቲያናችን ሰላሙን እንዲሰጠን የዘወትር ጸሎታችን ነው።

የምዕመናን ተወካዮች

ወስብሐት ለእግዚአብሔር


የሲያትል ገብርኤል ካህናት ወንጌሉን እያስተማሩበት ነው ወይስ እየነገዱበት?


 
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን::
“እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል” የሚባል የአባቶች አነጋገር አለ:: እንደተደበቁ መቅረት፤ እንደተሸፋፈኑ መቆየት፤ እንዳወናበዱ መቀጠል አይቻልም:: አንድ ቀን ያበቃለታል:: በጨለማ የዶለቱት በብርሃን ይወጣል:: በጓዳ የዶለቱት ኽሳሎን ብቅ ይላል::እንኳን ከህዝብ በስተጀርባ ይቅርና ከጓደኛ የሸሸጉት አፈትልኮ ያመልጣል:: እነሆ እውነቱ በሲያትል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ገሃድ ሆነ::
የሲያትል ቤተ ክርስቲያን ሃላፊ ስመ ጥሩ የሆኑትን ተወዳጅ መምህር አባ ገብረ ሥላሴ ጥበቡን ከአቡነ መልከ ጸዲቅ ጋር በመተባበር ከሲያትል ማባረራቸው ይታወቃል:: በዚህም ምክንያት የሲያትል ወጣትና ሕዝቡ ቅር ተሰኝቶ መምህር ገብረ ሥላሴ ጥበቡ ወደ ቦታቸው እንዲመለሱ ቢጠይቅ ሃላፊው “ምን እንዳትሆኑ ነው” ብለው አሻፈረኝ አሉ:: እንደራሳቸው የግል ካምፓኒ ሽምግልና አልፈልግም አሉ:: በዚህ ምክንያት የቤተ ክርስቲያኑ ታዛቢ ምእመናን ሶስት ደብዳቤዎች ጽፈን ተማጸንናአቸው:: ሃላፊው ግን ወይ ፍንክች የአባ ቢላዋ ልጅ አሉ:: ይቀጥላል…

ታደሰ የኋላእሸት አለምነህ የአሁኑ መላከ ብርሃናት ገብረስላሴ የኋላሸት አለምነህ ማን ነው?

ለምድ የለበሰ አስመሳይ የተኩላ ባህታዊ፤

መግቢያ

የኢትዮጵያ
 ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከሁለት ሽህ ዓመት በላይ ታሪክ ያላት ጥንታዊት ቤተክርስቲያን ስትሆን በኢትዮጵያ ታሪክ ዉስጥም ትልቅ ቦታ ይዛ የምትገኝ የታሪክ ደሴት ናት፡፡ ቤተክርስቲያኗ ጥንካሬዋን ጠብቃ የታሪክ ክብርና ሞገስ ሆና እዚህ እንድትደርስ ደግሞ ካህናትና መንፈሳዊ አባቶች የአንበሳዉን ሚና የተጫዉቱ ሲሆን  የቤተክርስቲያንዋ ዋና ምሰሶዎች በመሆን አስተምሮቷን  ሳይሸራርፉና ሳያዛንፉ በታማኝነት እየተቀባበሉ ዘመናትን አሻግረዉ ዛሬ ላይ አድርሰዋታል፡፡ የዛሬወቹ ባላደራወችም ይህንኑ የማስቀጠል ትልቅ መንፈሳዊ አደራ ከምንግዜዉም በላይ ተሸክመዉ ጉዞዉን ጀምሯል፡፡ ሆኖም ከቅርብ ግዜ ወዲህ በሚያሳዝን ሁኔታ ይችን ዘመናትን ተሻግራ ዛሬ ላይ መቆም የቻለች ቤተክርስቲያን ሊያደናቅፍና ስሟን ጥላሸት ሊቀባ የሚችል ፀያፍ ስራ አንዳንድ መንፈስ ቅዱስ ተገለጠልን በሚሉ በራሷ ሰዎች /ባላደራወች/ ሲፈፀም መታየት ጀምሯል፡፡እንዲህ እያደረግን ያለነው ቤተክርስቲያኗ ምን አይነት ምግባረ ብልሹነትእየተስፋፋባት እንደሆነች ለማሳየት ነው እንጂ እነርሱን በግል ለማሳጣት አይደለም።ይህን መደበቅ እና ማለፉ ጉዳቱ ለቤተ ክርስቲያን እንደሆነ ግልጽ፡ነው። 
ወደዚህ ሰው ታሪክ እንመለስ ታደሰ የኋላ እሸት አለምነህ ማን ነው?



ከዚህ ላይ ደግሞ አሜሪካ የዛሬ 2 እመት መነኮስኩ ብሎ........... መነኩሴ መስሎ ሲቀድስ (ጅብ በማያውቁት ሃገር ሄዶ ቆርበት አንጥፉልኝ ይላል አሉ......ወይ ማጭበርበር)

እንደ ታደሰ አለምነህ የኋላሸት አገላለጽ፤ ወላጆቹ ጋብቻቸውን ፈጽመው "የመጀመሪያ ልጅ ወልደው ደስ ብሏቸው ሳለ፤ ይኸው ልጅ በሕጻንነቱ ሲሞትባቸው፤ አሁንም ሁለተኛ ሲወልዱ ሲሞትባቸው፤ በመጨረሻ ሶስተኛ ልጅ ወልደው አሁንም ሲሞትባቸው" ይኼ የፈጣሪ ቁጣ ነው ብለው ተስፋ በመቁረጥ መኝታ ለይተው ይኖሩ እንደነበር ሁልጊዜ ይተርክልናል።  ታሪኩን በየጊዜው አዲስ ሰው ወደ ሲያትል ገብርኤል በመጣ ቁጥር ለዚያ አዲስ ሰው ስለራሱ ታሪክ ሲያወራ ይደመጣል።  በተጨማሪም እንደ ታደሰ አገላለጽ፤ እናቱ ለፈጣሪዋ ልጅ ከሰጠኸኝ አገልጋይ እንዲሆንህ ላንተ እሰጥሃለሁ እያለች ትሳል ስለነበር፤ እግዚአብሔር ጸሎቷን ሰምቶ አንድ በሃታዊ ከሩቅ ሐገር ከፈጣሪ ተልኮ ወደ ወላጆቹ መኖሪያ በመምጣት ወላጆቹን "እናንተ እስከ መቼ ድረስ አልጋ ለይታችሁ ትኖራላችሁ" ካለ በኋላ ለእናቱ ከእግዚአብሔር እንደተላከና እርሷም የተባረከ እና የተቀደሰ ልጅ ትወልጃለሽ እንዳላትና፤ ልጁም ካደገ በኋላ እናንተን ይጦራችኋል፤ አይዞአችሁ ተጽናኑ ተብለው እንደተነገሩ በራሱ አንደበት ሁልጊዜ ይነግረናል። "ራሱን ያጸደቀ ሰው"…. ምን እንበለው…መልሱን ለእናንተ ለአንባቢያን እተወዋለሁ።  ይህ በእንዲህ እንዳለ  ወላጆቹ ይህን መልእክት ከሰሙ በኋላ፤ ያንን የእግዚአብሔር ሰው ወደቤት ጋብዘው ከሸኙት በኋላ፤ ያችን ዕለት መኝታቸውን አንድ አድርገው አደሩ። በዚያች ሌሊት ታደሰ የኋላእሸት አለምነህ ተጸነሰ (አቤት ውሸት)። በ1949 ዓ.ም በደብረታቦር ፋርጣ ወረዳ ተወለደ። እናቱም ስለቷን ለቤተ ክርስቲያን መስጠት ስለነበረባት እርሱ (ታደሰ የኋላእሸት አለምነህ) ከተወለደ በሰባት አመቱ ለቤተክርስቲያን እንደተሰጠ ብዙ ጊዜ ሲናገር እንሰማዋለን። ከዚያስ …….
በሚቀጥለው ጽሑፍ ታደሰ የኋላእሸት አለምነህ እንዴት እንደተወለደ ከነሙሉ ታሪኩ ከቤተሰቦቹ ዘንድ ጠይቀን ስለ እርሱ ማንነት ጠንቅቀን አረጋግጠናል፤ በተጨማሪም ታደሰ አግብቷል ወይስ አላገባም? እንዴት አሜሪካ ሊመጣ ቻለ፤ ክህነቱ አለ ወይስ የለም? እነዚህን የመሳሰሉትን ጽሑፍ ይዘን እንቀርባለን  እናንተም ተከታተሉን፤
እውነት እና ንጋት እያደር ይጠራል የሚል የአባቶቻችን እነጋገር አለ…..


ይቆየን….