Saturday, 15 June 2013

ታደሰ የኋላእሸት አለምነህ ማነው?

የቀበሮ ባህታዊ? ዝርዝሩን እነሆ.....

*    ከአሜሪካ ወደ ሐገር ቤት በምን ምክንያት ተመለሰ፤ ስንት ጊዜስ ቆየ?
*    ባለቤቱንስ በሰላም አግኝቷት ይሆን?
*    አዲስ አበባ በሚኖርበት ወቅት ምን ይሰራ ነበር?
*   ስለ ታደስ የኋላእሸት አለምነህ የሕይወት ታሪክ ጉዳይ.....የታደሰ ታላቅ እህት ጸሐይ እና ታናሽ ወንድም ይርጋለም ያደረግነውን ቃለ መጠይቅ እነሆ.......

ክፍል ሦስት 

ታደሰ የኋላእሸት ባለቤቱን እሱ በፈለገው መልኩ ሆኖ ስላገኛት፤ ታማኝነቷን ጠብቃ በመገኘቷ ምክንያት….. ደስታው ከመጠን በላይ እንደሆነ ጸሐይ አብራርታልናለች።  እሱ ካነጸው ከተንጣለለ ቤት ውስጥ አብረው ለ7 ወር ከተቀመጠ በኋላ፤ ታደሰ በኖረባት በዚያች ሰባት ወር ውስጥ ትልቅ ቁም ነገር ሰርቶ መጣ…እሱም ለሌላኛው ወንድሙ እዛው ደብረታቦር ከተማ ……አንድ ቤት ገዝቶ…. ቁልፉን ካስረከበ በኋላ፤ የሥራ ጉዳይ…..የኑሮ ጉዳይ ነውና…..ባለቤቱን ለቤተሰቦቹ፤ ቤተሰቦቹን ደግሞ ለባለቤቱ አደራ ሰጥቶ…..ባለቤቱ አስማረችም እንዳትከፋበት….. ከማናቸውም በላይ መጀመሪያ ከገዛው ቤት ከወላጆቹ ጋር አብሮ ካስቀመጠ በኋላ… ባለቤቱ አስማረች በቤቱ ማዘዝ እንደምትችል ውል ሰጥቶ…… ጉዞውን ወደ ሲያትል እንዳደረገ በታላቅ እህቱ በጸሐይ አንደበት ተነግሮናል።   እኛም ልጅ ወልደዋል ወይ ብለን ጠይቀናት ነበር……. ምክንያቱም የ6 ዓመት ልጅ ከቤታቸው አለና።  እሱን እንኳ የማውቀው ነገር የለም አለችን…..ሕጻኑን እያየነው ለማናገር ያልጣርነው ጥረት አልነበረም….. ነገር ግን አልተሳካልንም።  ስለዚህ ሕጻን ልጅ ጉዳይ ጎረቤቶችን ጠይቀን ነበር….. የማን ልጅ እንደሆነ አናውቅም…… ልጁ የ 3 አመት ልጅ ሆኖ ነው ካስማረች ጋር የመጣው አሉን። ደጋግመን ጸሐይን እየጋበዝን ስለ ታደሰ ማንነት እና ልጁ የማን እንደሆነ እንድታስረዳን ጠየቅናት….. እርሷም  የተወሰነ ጊዜ ካንገራገረች በኋላ….. እውነት ምንጊዜም መውጣቱ አይቀር አለችና…….. አስማረችን በእርግዝናዋ ወቅት ባለቤቷ ታደሰ የኋላእሸትን ቦሌ ድረስ ሸኝታ…… በእንባ ተራጭታ…. ከተመለሰች በኋላ…….. መቀመጫዋን ባህርዳር እንድታደርግ እና ሆስፒታል እየተመላለሰች በቂ ህክምና እየተደረገላት እስክትወልድ ድረስ…… እዛው ባህርዳር እንድትቀመጥ በባለቤቷ በታደሰ ትእዛዝ አማካኝነት ተላለፈ።  እንደ ታላቅ እህቱ ጸሐይ አገላለጽ፤ አሜሪካ ከሄደም በኋላ በሳምንት ሁለት ጊዜ እየደወለ ስለ ጤንነቷ ይጠይቅ ነበር፤ እንዴ የተጎዳ ሰው መቼም ሁለተኛ ይጎዳ አይባልምና….አስማረችን ሁላችን ቤተሰቦች በሙሉ እየተመላለስን አንጠይቃት ነበር፤ ታናሽ ወንድሙ ይርጋለምም…. ባህርዳር ከሷ ጋር ሆኖ አብሮ እስክትወልድ ድረስ ተንከባክቦ እዚህ አድርሶለታል፤ እና ይሄ ባይታደል ነው እንጂ ሁለተኛ ልጁ ነበር….ግን ያለፈው አልፏል….አሁን ጥሩ ሁኔታ ነው ያሉት።  ታደሰም ባለቤቱ በሰላም መገላገሏን ስናበስረው….. ደስታው ከመጠን በላይ በመሆኑ ምክንያት…. አሜሪካ ያለው ሌላ ወንድማችን ከፍቅረ ድንግል የኋላእሸት ጋር አብረው ደጎስ ያለ ገንዘብ ተልኮ…3 በሬ ታርዶ…በደንብ ተደግሶ…. ነበር የልጁ ክርስትና የተከበረለት። የልጁ ስም ማን ይባላል ብለን ጠየቅናት….አባቱ (ታደሰ) ያወጣለት ስም ታደለ ታደሰ የኋላእሸት ይባላል አለችን።  የታደሰ እናት ለልጁ ያወጣችለት ስም “ሐዘኑን አሁን ገና ረሳ ስትል ደስታው ታደሰ የኋላእሸት ነው” አለችን።  ትምህርት ቤት ከገባ በየትኛው ስም ነው የሚመዘገብ? ብለን ጠይቀናትም ነበር….እንደ ጸሐይ አገላለጽ፤ ደስታው ይመስለኛል….ምክንያቱም ሁላችንም የወደድነው ደስታው የሚለውን ስም ነው…… ነገር ግን አባቱ ታደለ ተብሎ እንዲጠራ ስላዘዘ…… እስካሁን በሁለቱም ስም ይጠራል አለችን።  እንደ ጸሐይ አገላለጽ፤ ወንድሜ፤ በጣም ያሳዝነኛል….ለምን ተመላልሶ እንደማይመጣ ግልጽ አልሆነልኝም….እንዳንዴ ስለ እኔ ማንንም ቢጠይቃችሁ አትናገሩ ይላል….አንዳንዴ ደግሞ ወያኔ መምጣቴን ካወቀ ሊገድለኝ ስለሚችል ለማንንም ሰው የኔን ማንነት አትናገሩ፤ አንዱን ልጄንም ታስገድሉብኛላችሁ ይለናል….የሚገርማችሁ እሱ እኮ ማንንም አልገደለም…..ለምንድን ነው ወደዚህ የማይመጣው….እባካችሁን ንገሩት አይገድሉትም…..ባለቤቱም ብቻዋን እየተሰቃየች ነው ያለችው….አንድ ሰው ካገባ በኋላ አብሮ መኖር ተገቢ ነው…….. ግን እሱ ለምንድን ነው የሚፈራው? አሳምኑት እና በፈለገው ጊዜ እንዲመጣ ገፋፉት…..እኛም ቤተሰቦቹ ናፍቀነዋል….ማየትም እንፈልጋለን……ገንዘቡ ብቻ ምን ያደርግልናል ብላ ከእንባ ጋር ነገረችን…..እኛም የጠየቀችንን ጥያቄዎች ለታደሰ በጥንቃቄ እንደምናቀርብ እና ታደሰንም ገፋፍተን ለብዙ ጊዜያት የናፈቃቸውን ባለቤቱንና አንድ ልጁን ወደ አሜሪካ አምጥቶ የሚቀላቀልበትን ሁኔታ እንደምናመቻች ቃል ገባንላት......(ወደ አሜሪካ እንደተመለስንም አነጋግረነው ነበር ይህን ጉዳይ በሌላ ጽሑፍ እመለስበታለሁ)

በተጨማሪም፤ የታደሰ ታናሽ ወንድም ይርጋለምን ታደሰ አዲስ አበባ በነበረበት ወቅት ምን ያደርግ እንደነበር አነጋግረነው ነበር……እንደ ይርጋለም አገላለጽ፤ ታደሰ አዲስ አበባ በነበረበት ወቅት…. አዲስ ፍቅር፤ አዲስ አፍላ….ይዞት ስለነበር….. እኔን ከነመፈጠሬ የረሳኝ ጊዜ ነው…… ምክንያቱም አስማረችን የተዋወቀበት እና በፍቅር የከነፈበት ወቅት በመሆኑ ማንንም አያስታውስም።  በተጨማሪም ከሚያገለግልበት ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከአብዛኛው ምዕመን ጋር ይጣላል፤ ሰላምታም አይሰጣጡም…… ከካህናቱ ጋር ሰላም የለውም….በቅናት መንፈስ ይጣላሉ፤ ምን እንደሚያጣላቸው ግን ግራ ይገባኛል። በአጠቃላይ እርሱ ከአብዛኛው ካህናት ጋር ተጣልቷል ማለት ይቻላል….ከህዝቡም ጋር ቢሆን እንደዚሁ። አንድ ወቅት…. አባታችን እህል አስፈጭተህ ይዘህለት ወደ አዲስ አበባ ከታደሰ ዘንድ ሂድ ብሎ አዞኝ ነበር…እኔም እንደታዘዝኩት አድርጌ….. ትኬቴን ቆርጬ….. ወደ አዲስ አበባ ጉዞየን አቀናሁ…እንደደረስኩ እለቱ ቅዳሜ ነበርና ታደሰን አገኘሁት…..ታደሰም በደስታ አልተቀበለኝም…..ምክንያቱም …..እኔ ከቤተ ክርስቲያን ያሉት ካህናት ቤቱን አመላክተውኝ ስደርስ….እሱ እህቴ ናት ብሎ አስማረችን ለካህናቱ ሁሉ አስተዋዉቆ ነበር….ቅድስት ስላሴ የሚያገለግሉት ካህናት…. እኔን አስማረች የምትባል እህት አለቻችሁ? ብለው ጠይቀውኝ ነበር…..እኔም የለንም….አስማረች የሚባል ስም ጭራሽ ከቤተሰቦቻችን ውስጥ ማንም አይገኝም አልኳቸው…… እነሱም የአሽሙር ሳቅ ስቁብኝና……ማነው ስምህ አሉኝ….እኔም ይርጋለም የኋላእሸት እንደምባል ነገርኳቸው…. እነሱም ሊቀ ዲያቆናችን ባለጌ ነው….. እቃውን (መሽኝያውን) መሸከፍ ያቃተው ነውረኛ…..እግዚአብሔርን የሚዳፈር…..ሴት ልጅ እህቴ ናት እያለ….. እየደለለ የሚባልግ ባለጌ….አግብቶ በነጻነት ቢያደርግ አይሻለውም ነበር?……ቤተ ክህነት እንከሰዋለን….ከሚዋረድ ከዚህ ቢጠፋ ይሻለዋል…… ንገረው ብለውኝ ሄዱ።  እኔም በነገሩ ግራ ገብቶኝ ነበር….ስለማን እንደሚያወሩም አላወኩም ነበር……ታዲያ ያኔ ቤት ገብቼ ወንድም ጋሼን (ታደሰን) ካገኘሁት በኋላ…..ያመጣሁትን እህል አስረክቤ….. አልቦኝ ስለነበር ፊቴን እና እግሬን ታጥቤ የተወሰነ ሰዓት ካረፍኩ በኋላ…..ታደሰ ስለቤተሰቦቻችን ደህንነት ጠየቀኝ….በዚሁ አጋጣሚ ስለቤተሰቦቻችን ደህንነት ከተነጋገርን በኋላ…እሱም ሃዘኑን ረስቶ ደስተኛ መሆኑን ካረጋገጥኩ በኋላ….እኔም ደስ ብሎኛል ስለተጽናናህ አልኩት…..ምን ይደረግ ብለህ ነው እግዚአብሄር ሰጠ…እግዚአብሄር ነሳ አለኝ። እኔም ቀጠልኩና አስማረች የምትባል እህት አለህ ብለው ጠየቁኝ አልኩት….ታደሰ ግን ከመቀመጫው እንዴት እንደተነሳ አስደነገጠኝ…ብቻ ፍንጥር ብሎ ተነሳና ምን አልካቸው አለኝ….እኔም…በድርጊቱ ደንግጬ ወንድም ጋሸ ተረጋጋ ….እኔ ያልኳቸው…በፍጹም አስማረች የምትባል ጭራሽ በዘራችን የሚጠራ ስም የለም ብዬ ንግግሬን ሳልጨርስ አጎዛ….ዝተት….አንኮላ….ማንነቱን ለማታውቀው ሰው ዝምብለህ ትለፈልፋለህ እያለ ሲሳደብ እና ሲማታ አስማረች እንዳጋጣሚ ከተፍ አለች። (ከጋብቻ በፊት ሁለተኛ ባለቤቱን አሳምሮ ይደስቃት ነበር ማለት ነው አልኩ በልቤ……… አለበለዚያ እንደዚህ አያስደነግጠውም…….ምናልባት ያ ይሆን ወደ ኬንያ ያሰደደው? ወይስ ሌላም ጉዳይ ጭምር አልኩ በውስጤ እያንሰላሰልኩ……..እስኪ የጀመረውን ታሪክ ይጨርስልንና እነዚህን ጥያቄዎች ይመልስልናል)።  ከዚያስ አልነው ይርጋለምም ቀጠለና እንዲህ አለ……
ይቀጥላል……………
ታደሰ ወደ ኬንያ የሄደበት ምክንያት ምን ይሆን በሚቀጥለው ይጠብቁን




4 comments:

  1. በስመ አብ፤ ሰዓሊ ለነ፤ ምን አይነት ታሪክ ነው የምታስኮመኩመን ባክህ? እባክህን ይህንን ነገር አደባባይ አታውጣው? ለነገሩ በጽሑፉ እንደገለፅከው ሰውየውን ያናገራችሁት ይመስላል፤ ግን ምንም እንደማይመስለው ይታወቃል ምክንያቱም በቤተክርስቲያኑ ላለው ከፍተኛ ችግር ምንጩ እና ዋናው ታደሰ ሲሆን ያለው ችግር እንዳይፈታ ሁሉንም በር የሚቆልፈው እሱ እንደሆነ ሰምቻለሁ ስለዚህ አይሰማችሁም። እንግዲህ የቅዱስ ገብርኤል በተክርስቲያን ምዕመናን የሚሰግዱለት ሰው ማን እንደሆነ ከዚህ ፅሑፍ ተረድተው የራሳቸውን ማጣራት አድርገው ወደ አምላካቸው ንስሐ ይግቡ፤ የቤተክርስቲያኑ አስተዳደር እንዲስተካከል ከሚታገሉት ምዕመናን ጋር ትግሉን ይቀላቀሉ፧ አቤቱ አንደቸርነጥ ነው እና እስካሁን የጠበቅከን አሁንም ቸርነጥ አይለየን። ሰውየውንም የንስሓ ልብ ስጠው።

    ReplyDelete
  2. አቤቱ የሚያደርጉትን አያውቁም እና ይቅር በላቸው

    ReplyDelete
  3. ለነገሩ ብዙ የዚህ ዓይነት ታሪክ ያላቸው ሰዎች ስላሉ አልደነቅም፤ ቢሆንም የሲያትል ሕዝብ ይህንን ሰው ለምን ዝም አለ? በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ያለው ስልጣን ምንድን ነው? ይህን እያወቃችሁ እንዴት ዝም አላችሁ? ይህን ታሪኩን ለምን ለህዝቡ ይፋ አታደርጉትም?

    ReplyDelete
  4. St. Paul says: "Indeed, I wish everyone to be as I am, but each has a particular gift from God . . .Now to the unmarried and to widows I say: it is a good thing for them to remain as they are, as I do" (1 Cor. 7:7-8). He goes on to say: "An unmarried man is anxious about the things of the Lord, how he may please the Lord. But a married man is anxious about the things of the world, how he may please his wife, and he is divided" (1 Cor. 7:32-34).

    The Church has found it is better to keep priests moving from parish to parish every few years, perhaps for a few reasons, including the desire to prevent a cult of personality from building around a particular priest. This situation can put too much focus on the man rather than on the Gospel message. So, the Church prudently moves priests around. Can you imagine how much stress it would cause a priest to have to move his wife and family each time he is assigned to a new parish? Having a celibate priesthood also enables the bishop the full flexibility he needs to move priests around.

    this person needs counseling or help by a devoted father before he gets punished by God. i understand that he married twice but why is he acting like a monk? is he lying to God? what a fool. very stupid and nasty dud

    ReplyDelete