Wednesday, 12 June 2013

ታደሰ የኋላሸት አለምነህ ማን ነው?

የአሁኑ የቀበሮ ባህታዊ አባ መላከ ብርሃናት ገብረሥላሴ የኋላሸት አለምነህ....... ይሄ ዘለፋ አይደለም እውነተኛ ታሪክ ነው.....መልካም ንባብ!!!

ክፍል ሁለት
ታደሰ የኋላሸት አለምነህ አዲስ አበባን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲመለከታት አብረቅርቃ ስለታየችው፤ አልወደዳትም ነበር፤ እኔም በሆዴ አይ…የባላገር ነገር ብዬ ሳላስበው ጮክ ብዬ ተናገርኩ….…ወንድሙን ከልቡ አሳኩት፤ እኔም ደንግጨ ይቅርታዬን ጠየኩ……ጨዋታችንን ቀጠልን…..የታደሰ ታናሽ ወንድም ይርጋለምም ቀጠለና፤ ወንድም ጋሼ (ታደሰን) አዲስ አበባ ከሄደ በሶስተኛ ወሩ….. ወባ በሽታው ተነስቶበት ከሞት ስለተረፈ፤ ተሎ ፈጥኖ በመወሰን ጉዞውን ወደ ደብረታቦር ለመመለስ አቅዶ እንደነበርና፤ ያቀደውን እቅድ አባታችን ስላልተቀበለው፤ በአባታችን ምክርና ተግሳጽ ምክንያት እዛው አዲስ አበባ እየታከመ እንዲቆይ ሆነ።  
ታደሰ፤ በባለቤቱና ሳይወለድ ሕይወቱ በተቀጨው ልጁ ሞት ተጎድቶ ስለነበር፤ ሐዘኑም አዲስ አበባ ተከትሎት ስለመጣ፤ አጎታችንም የሱን ትካዜና ሐዘን ማስቆም ስለነበረበት….… ምክር ቢለግሰውም አልሰማ ስላለ…....ሁሉን ነገር እንዲረሳ በሚል ሃሳብ በፍጥነት የማታ ትምህርት ቤት አስገባው። ታደሰ በዲቁናው እያገለገለ ከሚያገኛትም ደሞዝ ለተወሰነ ወራት፤ ወለም ዘለም ሳይል ወላጆቹን ሲረዳ ቆይቶ፤ ሳያስበው ትምህርት ቤት አስማረች ዘለዓለም ከምትባል ወጣት ጋር በመተዋወቁ ምክንያት ለመጀመሪያ ጊዜ ድብን ያለ ፍቅር ይዞት ቁጭ አለ።  ወይ የባላገር ፍቅር አልኩ በልቤ…. ከዛም ይገርማል አልኩት ለይርጋለም….. እሱም በጣም እንጂ….….ወንድም ጋሼ (ታደሰን) ለመጀመሪያ ጊዜ ደስተኛ ሆኖ ስላየነው፤ ሁላችንም ቤተሰቦቹ በሙሉ ደስተኞች ነበርን።  አስማረችም ባህሪዋ መልካም ስለነበር፤ ወንድማችንን በደንብ አድርጋ ትንከባከበው ነበር፤ ምግብ እየሰራች ከቤቷ ትመግበው ጀመር….እሱም ለስድስት ወራት ያህል በተከታታይ ማክሰኞ…ማክሰኞ…. ሐዘኑን እንዲረሳ…. እየተባለ… ወደ ናዝሬት ከሌላኛው አጎታችን ከሚኖርበት ስፍራ በመሄድ፤ ለመዝናናት ትወስደው እንደነበርም ገልጾልናል። ከአስማረች ጋር ከተዋወቀበት ዕለት ጀምሮ፤ ለዘመዶቹ ያለው አትኩሮት ቀነሰ፤ ትንሽ ቆይቶም ወላጆቹን መርዳት አቆመ…….ጭራሹኑ ወላጆቻችን ለእሱ (ለታደሰ) ብቻውን እኮ ነው፤ ማን አለለት እየተባለ….. እህል ይላክለት ጀመር። እንደ ታናሽ ወንድሙ ይርጋለም አገላለጽ፤ ስለ ታደሰ ሁኔታ….. በእርግጥ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ነበር የተረዳሁለት….. ምክንያቱም የመጀመሪያ ፍቅር ከባድ ነው አለን። ታደሰ በዲቁና ሥራ እያገለገለ የሚከፈለውን ደሞዝ ምን ያደርገዋል? ብለን ጠየቅነው…… የታደሰ ታናሽ ወንድም ይርጋለም እንዲህ ሲል መለሰልን…..አዲስ አበባ ብዙ መዝናኛ አለ፤ ምንም የሚከፈለው ገንዘብ ትንሽ ቢሆንም………. ሴት ልጅ ከጓደኛዋ ጋር መዝናናትን ትወዳለች….የከተማ ልጅ እኮ ናት… ወዳጄ አለን…..እኛም እርስ በርስ ተያይተን ተሳሳቅን… ይርጋለምም ጨዋታውን ቀጠለ፤ እንዲህ ሲል……ስለዚህ ታደሰም ሐዘኑን በአስማረች ምክንያት ስለረሳልን ደስታችን ወሰን አልነበረውም። 
አንድ ነገር ግን የከፋን ነገር ነበር…ታደሰ ወደ ኬንያ ሊሄድ በተነሳበት ወቅት፤ አስማረች ጋር የቀለበት ስነ ስርዓት አድርጎ ነበር የሄደው፤ ነገር ግን እኛን ሳይጠራን….ሳይጋብዘን….ቤተሰቦቹ አልል ብለን…ዘፍነን ሳንድረው….እንዴት በጓደኞቹ በአገር ደብተራ ታጅቦ…በድብቅ ከአንዱ ጓደኛው ቤት ደግሶ… ቀለበት አድርጎ ይሄዳል……እኛን የገረመን ወላጆቹን እና አጎታችንን (ለዚህ ያበቃውን)፤ቤተሰቦቹን ከቀለበቱ ሥነ ሥርዓት ሳይጋብዝ በመቅረቱ፤ እጅጉን አዝነንበት እንኖር ነበር….ከጓደኛ ይልቅ ቤተሰብ ይበልጥ ነበር…. ነገር ግን ይሄን ያደረገበትን ምክንያት እስካሁን ድረስ ለእኔ እንቆቅልሽ ነው። እንደኔ…. እንደኔ…ይኼ ለእኛ ለቤተሰቦቹ ትልቅ ውርደት ነው፤ ምክንያቱም….. እኛ እሱን ለማስደሰት ደፋ ቀና እንላለን……እሱ በዚህ ክዶን ሄደ።  በዚህ ጉዳይ ተቀይመነው ነበር የምንኖር….. ነገር ግን በ2006 ዓ.ም ከ13 አመታት በኋላ ከአማሪካን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ...... በደንብ ደግሶ...... በእናቲቱ ማርያም ቤተ ክርስቲያን (ደብረታቦር).....  እኛን ቤተሰቦቹን ብቻ እንድናጅበው አድርጎ.......በቁርባን ጋብቻውን  አጽንቶ፤ እኛንም ስላስደሰተን ይቅር ብለናል አለ። (እኔም በውስጤ ከራሴ ጋር እየተነጋገርኩ በመገረም፤ ሁለተኛ ትዳር ይሉሃል ይሄ ነው፤  አይይይ... የታደሰ ክህነት ከፈረሰ ለካ ቆይቷል አልኩ..... ነገር ግን ድርጊቱ እስከ አሁን ድረስ ይገርመኛል)
ከእኔ ጋር አብሮኝ የሄደ አንዱ ጓደኛዬ የታደሰ ታላቅ እህቱን ጸሐይን እንዲህ ሲል ጠየቃት….አንችስ….. ከቀለበቱ ስነ ስርዓት ተጋብዘሻል ወይ? የታደሰ ታላቅ እህት ጸሐይም በቁጣ መንፈስ እንዲህ ስትል መለሰችለት….ወይ መጋበዝ……እሱ በድብቅ አድርጎት ነው እኮ ወደ ኬንያ የሄደው….በዚህ ምክንያት ወላጆቻችን በጣም ያዝኑበት ነበር…”ልቡ የማይገኝ፤ እሾህ፤ ይለው ነበር አባቴ”…. ምክንያቱም እሱን ለዚህ ያበቃው አባቴ ነበር። ቢሆንም…በቤተክርስቲያን ሰዎች እና በካህናቱ ላይ ከተንኮለኞች ደብተራ ጋር አብሮ ያደርገው የነበረው ክፋት እና ተንኮል… በሽታ ላይ ጥሎት ብዙ ያንገላታው ነበር።  አስማረችንም እኮ ቀለበት ካደረጉ በኋላ በጓደኞቹ ደብተሮች አስተብትቦ ለ13 አመት እንድትጠብቀው አድርጓል፤ እሷ ግን እጅጉን ታሳዝነኝ ነበር..አትሰራም…አትማርም…. እንዲሁ ብቻ የቤት እመቤት ሆና ቀርታ ነበር። ቢሆንም መጥቶ ጋብቻውን ስላጸናላት ደስ ብሎኛል፤ አሁን ግን ከእኛ ወላጆች ጋር አብራ ትኖራለች። እግዚአብሔር ይመስገን ለዚህ ላበቃቸው፤ በፊት ግን በጣም አዝኜበት ነበር በማለት ትዝታዋን አጫውታናለች።
ይገርምሃል አለች ጸሐይ….ታደሰን ወደዚህ (ኢትዮጵያ) እንዲመጣ እና እንዲያየን ብዙ ጥረት አድርገን ነበር፤ ነገር ግን  የእርሱ መልስ ሁልጊዜ አንድ አይነት ነበር… “ወያኔ ይገለኛል”… ለምን እንደዚህ እንደሚለን ግን አይገባንም ነበር…..አባታችንም ታደሰን ምን አርገሃል ወያኔ የሚገድልህ ብሎ ደጋግሞ ጠይቆት ነበር፤ታደስ ግን ጥያቄውን መልሶለት አያውቅም..... እንዲሁ ብቻ ብዙ አመት ባለቤቱን ትቶ ተቀምጦ ነበር…ቢሆንም አስማረች ለአባቴ እንዲህ አለችው….እኔ እንግዲህ ሌላ ላገባ ነው….. 13 አመት ጠብቄአለሁ….. ከእንግዲህ ወዲህ ዘር መተካት አለብኝ፤ እድሜዬ ከፍ እያለ ነው.....እሱ ዘንድሮ የማይመጣ ከሆነ… ሌላ አገባለሁ በማለቷ ምክንያት… የታደሰ እናት በፍጥነት ለታደሰ አሜሪካ ድረስ በመደወል….. እንግዲህ እኔ እንደምታውቀው መንኩሻለሁ…አርጅቻለሁ….በጣም አሞኛል…..ከመሞቴ በፊት ፊትህን ልዬው፤ ልባርክህ እና ልሙት ብላ ለታደሰ ትነግራለች……ታደሰም የእናታችንን ቃል ሰምቶ፤ በፍጥነት እዛው እናንተው አካባቢ የሚኖር (ሲያትል) ቴዎድሮስ ከሚባል ልጅ ጋር  በኬንያ አድርገው ደብረታቦር መጡ፤ ያን ጊዜ አስማረች ባለቤቷ ይመጣል ብላ ባላሰበችበት ሰዓት በአካል ስላገኘችው፤ ደስታዋ ከመጠን በላይ ስለነበር፤ ራሷን ስታ ነበር… አስማረችም እንደነቃች ከባሏ ከታደሰ ጋር ያላትን ናፍቆት እንድትወጣ ከእርሱ ጋር ተዋት….. ከዚያስ............................................................................


ከታደሰ የኋላእሸት አለምነህ ታላቅ እህት ጸሐይ ጋር የነበረንን ቆይታ እንመለስበታለን፤ በታደሰ ሕይወት ዙሪያ ከታናሽ ወንድሙ ከይርጋለምም ጋር የነበረንን ቃለ መጠይቅ ማለትም ታደሰ አዲስ አበባ በነበረበት ወቅት ምን እንደሰራ……... ወደ ኬንያ ለመሄድ ያነሳሳው ምክንያት ምን እንደነበር………ወደ አሜሪካ በምን ምክንያት ሊመጣ እንዴት እንደቻለ በሚቀጥለው ክፍል ይጠብቁን………

10 comments:

  1. wow, please add part three soon....it is fantastic article

    ReplyDelete
  2. ለምንድን ነው እንደዚህ ያለውን የግል ገበናውን አደባባይ ላይ ማውጣት ያስፈለገው? እንደሚታወቀው እና እንደምንሰማው በቅርቡ ቅዱስ ፖትርያርኩ ከሚሾሙት ፭ አዳዳስ ጳጳሳት አንዱና በ፩ኛ ተራ ቁጥር የተቀመጠው እሱ ነው እና ይሄ ጉዞውን አያደናቅፍም ትላላችሁ? የሚገርም ነው በቤተክርስቲያናችን ያሉት መነኮሳት እና ጳጳሳት ታሪካቸው አንድ መሆኑ እና በቤተክርስቲያናችንን ማሰደባቸው፦ አቤቱ ይቅር በለን፤

    ReplyDelete
  3. what is next? it is very interesting story

    ReplyDelete
  4. ሲያትል ቅዱስ ገብርኤል ያለው አብዛኛው ሰው የዋህ ከመሆኑ የተነሳ እዛው ያሉትን አባቶች ማምለክ ጀምረዋል፤ ስለዚህ ይህንን መስማት አይፈልጉም ወዳጄ፣ እግዚአብሔር አምላካቸውን እንደነሱ አይፈሩትም ብቻ ለቤተክርስቲያናችን የሚሆነውን ሰላም ይስጠን።

    ReplyDelete
  5. ልክ ብለሃል በርግጥ አሜሪካ ጳጳስ ለመሆን መስፈርት የለውም፤ ለጵጵስና የሚታጭ ሰው ምን መሆን አለበት ትላላችሁ? ታሪኩና ማንነቱ ሳይረጋገጥ ዝምብሎ እንዲሁ እንደ ጊፍት መስጠት....ጵጵስና የረከሰበት ዘመን ....

    ReplyDelete
  6. እባክህን ሰርዘው

    ReplyDelete
  7. የሚገርም ታሪክ ነው ጎበዝ፦ ለዚህ ነዋ ሰውየው እየተናደፈ ሰው የማያስጠጋው እና ብቻውን አድራጊ ፈጣሪ የሆነው? እኔ የሚገርመኝ በዙሪያው የተሰገሰጉ ጥቅመኞች ህሊና ቢስ መሆናቸው ብቻ ነው ለነገሩ ዶላር የማይቀይረው ነገር አለ ብላችሁ ነው። ለሁሉም መጨረሻው ይናፍቃል።

    ReplyDelete
  8. Hey we need to here part 3........

    ReplyDelete
  9. we would like to hear part three please ላባችንን አንጠለጠላችሁት እኮን

    ReplyDelete
  10. Hey can you post part 3 for this weekend gift.....

    ReplyDelete