Tuesday, 18 June 2013

ታደሰ የኋላእሸት ማን ነው? እውነተኛ ካህን ወይስ ምን..............

ክፍል አራት
*   በ1982 ዓ.ም አዲስ አበባ፤ ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ በታደሰ እና በአስማረች ዙሪያ ላይ ምን ውሳኔ አስተላለፉ?
* ታደሰ በፍጥነት ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ ሊሰደድ የቻለበት ምክንያት ምን ይሆን?
*  ታደሰ ወደ ኬንያ በሄደበት ወቅት ምን ተፈጠረ?
*  ታደሰ ደብረ ዘይት ያነጸው ሕንጻ ለማን ይሆን?
እንደ ታደሰ ታናሽ ወንድም ይርጋለም የኋላእሸት አገላለጽ….ወንድም ጋሼ (ታደሰ)… እንደዚያ ሲሳደብ እና ሲማታ….አስማረች መጣች….ከዛም ሆድዬ ለምንድን ነው እንደዚህ የምትናገር ውጭ ድረስ እኮ ትሰማለህ አለችው………እኔንም...... ይርግዬ አይዞህ ምን እንደዚህ የሚያስጮህ ነገር ተገኘ አለችኝ?  ታደሰም...... እነዚያ ምቀኞች ናቸው..... ስለ አንቺ እና ስለ እኔ ማንነት እየመረመሩት..... አላት ለአስማረች……. አስማረችም እኔን ምን አልካቸው ብላ ጠየቀችኝ..... እኔም እሷን (አስማረችን) ቤተሰባችን አይደለችም….. በዘራችን ውስጥ እንደዚህ አይነት ስም የለም ብዬ አስረዳኋቸው….የምናገረውን ሳልጨርስ አቋረጠችና....ሌላ የነገርካቸው ነገር የለም አለችኝ…በፍጹም አልኳት….. ስለ እኔና ታደሰ እጮኝነት አልነገርካቸውም አለችኝ፤ በፍጹም አልኳት….ተመስገን….ተናግረህ ቢሆን ኖሮ….እንጇ....በወንድምህ ሕይወት ላይ ነበር የፈረድክበት አለችኝ....ግራ ገባኝ...ቀጠለችና.....ዛሬውኑን ከስራ አፈናቅለኸው ነበር አለችኝ። ከተወሰነ ሰዓት በኋላ የቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ..... የሰበካ ጉባኤ አባላት በሙሉ....... እና የተወሰነ የቤተክርስቲያኒቱ አባላት ሆነው...... ታደሰ ካለበት ቤት መጡ።  እኔም የአመጣጣቸው ሁኔታ አልጣመኝም ነበር…..ወንድም ጋሼም (ታደሰም) እኔን ውጭ እንድቆይ ጠየቀኝ….እኔም ውጭ የወጣሁ መስዬ....... ተደብቄ ነገሮችን ማዳመጥ ጀመርኩ…..ነገሩን ያነሱት የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪው አባት ናቸው….በእድሜ ዘለግ ያሉ አባት ናቸው…..ወንድም ጋሼን (ታደሰን)…እባክህን ልጄ ሳትደብቅ አንድም ነገር ሳትሸሽግ ንገረኝ……እውነታው ምንድን ነው? ምንድን ነው የምሰማው? ለዚህች ልጅ ቀለበት አስረህላታል? ታደሰም…አላሰርኩም እንዳይል...... ከቀለበቱ ስነ ስርዓት ከነበሩት ጓደኞቹ መካከል አንዱ........ ከሳሽ ሆኖ ተገኝቷል….የፎቶ ምስልም አቅርቦለታል….ታደሰ ባላሰበው ሁኔታ ቪዲዮ ቀድተውት ስለነበር…. ይህን ጉድ ለወላጆቼ ሰምተው ከሚያፍሩብኝ......... ምነው አፈር በበላኝ እያለ ሲናገር.... እሰማው ነበር…አስተዳዳሪውም ከዛሬ ጀምሮ ቅዳሴ እንዳትገባ....ንስሐ ግባ....ለምን ፈጣሪህን ትዳፈራለህ? ቤተክርስቲያንን ለምን ታረክሳለህ.....ይህንን ጉዳይ ሕዝብም...... ቤተክህነትም ማወቅ አለበት ይሉት እንደነበር ሰምቻለሁ.....ወንድም ጋሼ ግን ፈጽሞ ይማጸናቸው ነበር.....ሰው አይስማ እባካችሁን....... እኔ ግን ሌላ ስራ እፈልጋለሁ...... ይል እንደነበር አስታውሳለሁ..... ነገር ግን እሁድ እለት..... ሰዎች ከቅዳሴ በኋላ የታደሰና የአስማረችን ጉዳይ...... ወሬውን አስተጋብተውት ስለነበር....... ብዙ ሰው ወንድም ጋሼን ይሰድበው እና ያንቋሽሸው ነበር....ስለዚህም ሸሽቶ ወደ ኬንያ ሄደ.......እኔ ግን የማይገባኝ ነገር ቢኖር.......... ትዳር ከፈጣሪ ነው ይባላል….ወንድም ጋሼም ቀለበት ቢያስር ምንድን ነው ሐጥያቱ? ምንድን ነው ችግሩ፤ በወንድም ጋሼ (ታደሰ) ላይ ስለቀኑበት.....አሳደዱት...... እሱም ተሰድዶ ሔደላቸው……ያው እነሱ ይፈሩ እንጂ እሱስ መጥቶ ሰርጉን ሰርጎ….በክብር አግብቶ ተመልሷል….እንዲያውም ከሃብት ላይ ሃብት ያለው ሰው ሆኗል.....ትእግስትን ቢያጣ እግዚአብሔር አስማረችን ሰጥቶታል፤ እግዚአብሔርም ባርኮታል...ይሄ ሁሉ ሃብት የበረከት ውጤት ነው....ከዚህ እንደዚህ ሲያሳድዱት የነበሩት አሁንም ድረስ እያከኩ ይገኛሉ አለን።  እኛም...... የወንድምህ የታደሰ ታሪክ በጣም ያሳዝናል….ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፏል አልነው….እሱም ወንድም ጋሼ መች በዚህ አበቃ…..ኬንያ ሲሄድ እኮ..... የኔን ታላቅ ወንድም ፍቅረን ከደብረታቦር ወደ አዲስ አበባ አስመጥቶ....... ከአስማረች ጋር እንዲቆይ አድርጓል። ደግሞም ፍቅረን መጀመሪያ ወደ አሜሪካ የወሰደው ወንድም ጋሼ ነው……ፍቅረድንግል አሜሪካ እንዴት ሊመጣ ቻለ አልነው?  ወንድም ጋሼ የጻፈው ደብዳቤ አለ...... ላሳያችሁ ብሎ አሳየን......በዚህ መመሪያ ተከትሎ ነው አሜሪካ የገባው...አሜሪካ (ሲያትል ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሲመረቅ....ዲያቆን ነኝ በልና ደብዳቤ አስጽፈህ ቤተ ክህነት ግባ አለው...ወንድም ጋሼ እንዳዘዘው አደረገ.....ፍቅረንም ያለምንም ውጣ ውረድ ሊውስደው ቻለ አለን። ፍቅረ ድንግል የኋላእሸት ግን ምንም ክህነት እንደሌለው ዓለም ያውቃል።  (ደብዳቤውም በእጃችን ይገኛል....) የታደሰ ታናሽ ወንድም ይርጋለምም እንዲህ አለን...እኔ ተስፋ አልቆርጥም....የማይቻለውን የፍቅረን ጉዳይ አስፈጽሞ የወሰደ የባለቤቱን እና የልጁን ያቅተዋል ብየ አልጠረጥርም...በዚህ ሃብት አለ... አንድ ቀን ፈጣሪ ሁሉንም ሲያስትካክል..... እሷንና ደስታውን ይወስዳቸዋል።  አሁን ለአስማረች እና ለደስታው ደህንነት ሲባል ደብረ ዘይት አንድ ትልቅ ዘመናዊ ባለ 4 ፎቅ ግቢ ሌላኛው ወንድማችን ፍቅረድንግል የኋላእሸትን ልኮ ቤት አሰርቶላቸዋል። ደብረታቦር ያለው ቤትስ ብለን ጠይቀነው ነበር።  ደብረታቦር ሁለት ቤት ሰርቷል….አንደኛው ቤት ለሌላው ወንድማችን ሃላፊነቱን ሰጥቶት ይኖርበታል…… ሌላኛውን ቤት ደግሞ ለወላጆቹ እዛው ደብረታቦር ላይ ገዝቶ አስረክቧቸዋል።  ምንም እንኳ የወንድም ጋሼ ባለቤት አስማረች እና ደስታው ከወላጆቻችን ጋር ቢኖሩም.......... አሁን ግን ደብረዘይት ውስጥ ተሰርቶ ያለቀው ቤት ውስጥ እንዲኖሩ በወንድም ጋሼ ትዕዛዝ ተላልፏል። እኛም ይህን ያደረገበት ምክንያት ምን ይሆን ብለን ጠይቀነውም ነበር…..ይርጋለምም……ስለ ወንድም ጋሼ (ስለ ታደሰ የኋላእሸት) ማንነት ሰው ከጠየቃችሁ አናውቅም በሉ ይለን ስለነበር….እንደዚህ የሚለን ሁኔታዎች ወይም የማይነገረን ሚስጥር ምንድን እንደሆነ ግልጽ ካለመሆኑ የተነሳ..... ነገሩ ግልጽ እስኪሆንልን ድረስ..... የሚመለከተን ነገር የለም ብለን መልስ ከሰጠነው ወዲህ........ነገሮችን ወይም ያለውን ሚስጥር እንኳ ሊገልጽልን ስላልፈቀደ….ባለቤቱን እና ልጆቹን ደብረዘይት ከሰራው አዲስ ቤት እንዲኖሩ አዟቸዋል....ለእኔ ደግሞ ይሄ ነገር ውስብስብ ብሎብኛል...ምኑ እንደሚያስጨንቀውም ግራ ገብቶናል አለን…..ደብረዘይትም ሔደን ቤቱን ተመልክተናል…..መቼስ ይህ ሁሉ ገንዘብ የት እንደመጣ እግዚአብሔር ይወቅ…..በእግዚአብሔር ገንዘብ መቀለድ መልካም አይደለም…..የቤተክርስቲያንን ገንዘብ መዝረፍ እና መመንዘር ውጤቱ መጨረሻው አያምርም…. ያን ሁሉ ቤት እንዴት ሊሰራ ቻለ? አዲስ አበባ ቦሌ ላይ ያለውን ቢዝነስስ እንዴት ሊገዛ ቻለ? ደብረታቦር ውስጥ የጄኔሬተር አከራይ ዋና ቢዝነስ እንዳለውም አረጋግጠናል…ይህ ሁሉ ገንዘብ የት መጣ? …..አንባቢ ግን ይህ ሰው ታደሰ የኋላእሽት ማን እንደሆነ ያስተውል…..ሌባ ከሌብነቱ አይዘልምና ይብቃ እንበል…….ለማንኛውም ይህንን ጉዳይ በተመለከተ እመለስበታለሁ።

በ1982 ዓ.ም ታደሰ የኋላእሸት ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ የሄደበት ወቅት ነበር። በዚያን ወቅት የደርግ ዘመነ መንግስት በወያኔ እየተገረሰሰ የመጣበት ወቅት ነበር። እንደታደሰ አገላለጽ፤ አባቶች ጳጳሳት እሱን ኬንያ አስቀድሞ በመሄድ…. ቦታ አዘግጅቶ እንዲጠብቃቸው በጥብቅ መታዘዙን እና ሄዶም ብቻውን ከኬንያ አምባሳደሮች ጋር በመነጋገር....... ለአቡነ መርቆሬዎስ፤ አቡነ ኤልያስ እና አቡነ ዜና ማርቆስ፤ መልካም ቦታ አዘጋጅቶ እንደጠበቃቸው ሁልጊዜ ሲናገር ይደመጣል።  እውነታው ግን እንዲህ ነው፤ አዲስ አበባ ከሚኖረው አጎቱ ጋርም ስለ ታደሰ ጉዳይ ተነጋግረን ነበር……እንደ ታደሰ አጎት አገላለጽ፦ ታደሰ ወደ ኬንያ ሃገር እንደሌላው ዜጋ ተሰዷል፤ ወደ ኬንያ በተሰደደበት ወቅት…… ታናሽ ወንድሙ ፍቅረ ድንግል የኋላእሸት…… ከእኔ ጋር ለተወሰነ ጊዜ ቆይቷል…… ቢሆንም ታደሰ ከተሰደደ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ….. የተወሰኑ አባቶችም ወደ ኬንያ ሲሰደዱ……ታደሰ እንደሌሎች ስደተኞች…. አብሮ የተሰደዱትን አባቶች ተቀብሏል…… ቢሆንም አዲስ አበባ በነበረበት ወቅት....... አንዲት እናት ልጄ ዘመናዊው ትምህርት አልገባት አለ....... በማለት ታደሰን ታማክረዋለች፤ ታደሰም...... እኔ አንድ ነገር እሰራላትና (እጸ ፋሬስ)...... ትምህርቱ በቀላሉ እንዲገባት ይሆናል የሚል ተስፋ ቃል ሰጣት....ይህንንም ካላት በኋላ....... ደጎስ ያለ ገንዘብ እንድትከፍለው አስጠንቅቆ ነገራት…… እናትየዋም ልጄ ትምህርቱ ገብቷት..... እንደሌላው ሰው ብትመረቅልኝማ....... አንተ ያልከውን ገንዘብ እከፍላለሁ...... ብለው ታደሰና ሴትየዋ ይስማማሉ።  ታደሰም ስራስሩን (ዕጸ ፋሬስ) ወይም እጀሰብ መድሃኒት (በዘልማድ የሃበሻ መድሃኒት ...የጥንቆላ መድሃኒት) ተብሎ የሚጠራውን አድርጎ…ይህን ማታ ከመኝታ በፊት…… እህል በልታ ትጠጣና ተሸፋፍና ትተኛ... ሃይምሮዋ ብሩህ ይሆናል...እመኝኝ ብሎ ለእናትየዋ እጸ ፋሬሱን ይሰጣታል…. እናት ደግሞ..... ልጄ ትምህርቷን ልታጣድፈው ነው እንግዲህ በማለት..... ስለ ልጇ የወደፊት ተስፋዋን ሰንቃ....... ለልጇ  ታደሰ የኋላእሸት የሰጣትን ያንን የቅጠላቅጠል እና የሥራሥር ጭማቂ የመሰለ ነገር ታጠጣታለች……መድሃኒቱም ሃይሉ በዝቶ ስለነበር....... በደሟ ውስጥ ስለሰረጸ (ስለገባ) መርዟት ሞተች……የዚህን ጊዜ ታደሰ በተፈጠረው ክስተት የተነሳ....... የነፍስ ተጠያቂ ከመሆኑ በፊት....... ወዲያውኑ ሳያወላውል ወደ ኬንያ ተሰደደ።  እንደ ታደሰ አጎት አገላለጽ፦ ታደሰን ወደ አዲስ አበባ አምጥቼ ለዚህ ያበቃሁት እኔ ነበርኩ….. ነገር ግን ለብዙ ዘመን በኖርኩበት ሃገር ተዋርጄ...... ተሳቃቄ  እንድኖር አድርጎኛል..... የጎረቤት መዘባበቻ...... መሳቂያ መሳለቂያ አድርጎኛል...ይህ ነገር ከተፈጠረ ወዲህ ብዙ ሰው ለብዙ ጊዜ መጠቋቆሚያ አድርጎኝ ነበር..... እሱ ነው የደበቀው እየተባልኩ መከራየን አይቼ ነበር....... አሁን ግን ሁሉም ነገር ተረስቷል ከ20 አመት በላይ ሆነው...... ለዚህም እግዚአብሄር ይመስገን እኔ ምንም ያደረኩት ጥፋት አልነበረምና አሉን ።  በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን ድረስ እንዳዘነቡትም ነግረውናል…….ነገር ግን ታደሰ በ2006 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ በተመለሰ ጊዜ..... ሰርጉ ሊሆን ሳምንት ሲቀረው….. ታደሰ አጎቱን ስላደረገው ስህተት ይቅርታ እንደጠየቃቸውም አጫውተውናል።  እኛም ታደሰ ወደ ኬንያ ከመሄዱ በፊት..... ለአስማረች ቀለበት አድርጎ እንደነበር........ በታናሽ ወንድሙ በይርጋለም አማካኝነት የተነገረንን ጠይቀነው ነበር።  የታደሰ አጎትም……አወ ቀለበትማ አድርጎ ነበር የሄደው….ነገር ግን በትእግስትዬ ሞት በጣም አዝኖ ነበር…ቢሆንም በአስማረች ዘለዓለም ደግሞ በደንብ ተጽናንቷል…. በፈረንጆች አቆጣጠር በ2006ዓ.ም በደንብ ደግሶ ቤተሰቦቹን ብቻ እንድናጅበው አድርጎ…..አስደስቶን ነበር ወደ ሃገሩ የተመለሰው አሉን። እኛም ታደሰ ኢትዮጵያ በመጣ ወቅት እነዚያ የሟች ቤተሰቦች እንዴት አልፈለጉትም ብለን የታደሰን አጎት ጠይቀነው ነበር? የታደሰ አጎትም…. ታደሰ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ..... አንድ የተባረከ ልጅ ቴዎድሮስ ከሚባል ጋር በኬንያ አድርገው  ነበር የመጡት...... ቴዎድሮስም ነገሮችን ሁሉ ይከታተልለት ነበር….ሁልጊዜ ከሱ ጋር አብረው ነው የሚወጡትም የሚገቡትም....... ደግሞም በድብቅ ስለሆነ የመጣው...... ከቤተሰብ በቀር ማንንም አያውቅም…. ሰርጉንም ቢሆን እኮ እኛ ቤተሰቦቹ ብቻ ነን የተጋበዝነው አሉን....... እኛም ታሪኩ እውነት መሆኑን አረጋገጥን።  

ታደሰ፤  አዲስ አበባ በነበረበት ወቅት…. ምን አይነት ስራ ይሰራ እንደነበር…..ብዙ ታሪኮች አሉ፤ ነገር ግን አሜሪካ ላይ ከሚሰራቸው ስራዎቹ ጋር አብረን ጣልቃ እያስገባን እናስነብባችኋለን ተከታተሉን።

ታደሰ ወደ አሜሪካ ከመጣ በኋላ ያለውን ታሪክ በሰፊው እዘረዝረዋለሁ ይጠብቁን…………

19 comments:

  1. በጣም የሚገርም ታሪክ ነው። ሰዓሊ ለነ አንቺ ቤተክርስቲያን ስንቱን ጉድ ነው የቻልሽው?????

    ReplyDelete
  2. ትክክለኛ መረጃ ከሆነ ለምን ይሔ ነገር ለቅዱስ ሲኖዶሱ አይቀርብም? ለምንስ ለሲያትል ምዕመናን በግልፅ አይነገርም??? ይሔ ሰው እኮ ለጳጳስነት የታጨ ነው ጎበዝ፣

    ReplyDelete
  3. ከወራት በፊት አንዱን ዲያቆን በቦክስ ሶስቴ አይኑ ስር ተማትቶ የሚቀድስ ጀግና፤ ወይ ጳጳስ፤ ርካሽ ሰው ነው። ስድብ በአንደበቱ የተሞላ ሆኖ ሳለ በዛ ላይ ደግሞ ተንኮሉ ተጨምሮበት ብቻ ቤተክርስቲያኑ በሱ እየተበጠበጠ ይገኛል፤

    ReplyDelete
  4. እንዴት ነው አሜሪካ ተቀምጦ በቦክስ መማታት? ይሔ ሊሆን አይችልም ግን ደግሞ ምን ይሳነዋል ሰውየው ብላችሁ ነው፦ የሲያትል ገብርኤል አብዛኛው ምዕምን እንደሆነ ለሰውየው የሚገዛ ነው። ወይ ታሪክ ሰው ማምለክ ይሉሃል እንዲህ ነው። እግዚአብሄር ስራውን የሚሰራበት ግዜ አለው፥ እውነቱ እየወጣ ነው ገና ብዙ እናያለን እንሰማለን፤

    ReplyDelete
  5. We are waiting next part (5), please release.....thanks

    ReplyDelete
  6. አባ ገብረ ሥላሴ በአሁኑ ሰዓት ሲያትል የሚያደርጉትን በአግባቡ አላውቅም። ከሰው ጋር የመግባባት ችግር ሊኖርባቸው ይችል ይሆናል። ይህ በዚህ ጽሑፍ የቀረበው ታሪክ ግን ፍጹም ልብ ወለድ ነው። ጸሐፊው ሰውን ባይፈሩ እግዚአብሔርን ሊፈሩ ይገባል። የሌለን ታሪክ መጻፍ አግባብ አይደለም። "አትግደል" የሚለውን ትዕዛዝ እየተላለፉ ነው። ምንም እንኳ የአባ ገብረ ሥላሴን ነ ፍስና ሥጋ ባይለዩትም አባን እየገደሉ ነው ያሉት። ለነገሩ ተሳዳቢ በመሳደቡ ተሰዳቢው አይሞትም እንዲያውም ክብር ያገኙበታል። እባካችሁ የግል ጥላቻን ለመወጣት ብለን ያልሆነ ታሪክ አንጻፍ። መቅሰፍቱ ለእራሳችን ነው። በሰላምም አያስተኛም። እናስተውል እንጂ ጎበዝ።

    ReplyDelete
  7. አባ ገብረ ሥላሴ በአሁኑ ሰዓት ሲያትል የሚያደርጉትን በአግባቡ አላውቅም???? ብለው አስተያየት የሰጡት አባት እሱ ሲያትል ምን እንደሚሰራ ካላወቁ ታዲያ የት የሚያውቁትን ነው ታሪኩ ልብ ወለድ ነው የሚሉት? ሊሆን ይችላል ግን ሃሳብዎት ይጋጫል። ይልቅስ እንዲህ በሚለው እንስማማ ማንም ሰው ዝም ብሎ የሰውን ስራ በፈለገው መልኩ መግለፅ ማለትም አንደዚህ ባለው መልኩ ማውጣት አግባብም አይደለም፤ ነውርም ነው፤ በተለይ የሚያወጣው ሰው የቤተክርስቲያን ሰው ከሆነ ቤተክርስቲያን እንደዚህ አታስተምርም ስለዚህ በዚህ መልኩ ሃሳብህን አትግለፅ እላለሁ፤ ጠቀሜታው ስለማይታየኝ፤ ግን ታደሰ ይህንን አያደርግም ብየ አልስማማም ምክንያቱም ከዚህ ታሪክ ውስጥ ጥቂቱ እውነት እንደሆነ ስለማውቅ።

    ReplyDelete
    Replies
    1. ምነው ግራ ተጋቡ? የተጻፈው ታሪክ በሲያትል የተፈጸመ አይደለም። በአዲስ አበባና ኬንያ ከብዙ ዓመታት በፊት ተፈጸመ ነው የሚለው። አስተያየት ሰጪው ደግሞ በሲያትል የሆነውን አላውቅም በአዲስ አበባና በሌሎች ሆነ የምትሉት ግን ትክክል አይደለም ነው ያሉት። የምን ማምታታት ነው? ነገሩማ የስም ማጥፋት ዘመቻ ስለሆነ አንዴ የገደለ ሁለተኛ መግደል ሀጢያት መስሎ አይታየውም ይባላል። ስለዚህ የሚፈጸመው ስህተት ሁሉ ለደራሲው አይታየውም። እባክህ በፈጠረህ አምላክ እውነት ያልሆነውን አትጻፍ። እውነት ካለህ ሰውየውን ፊት ለፊት ግጠመው ቤተ ክርስቲያንንም ትጠቅማለህ። ለነገሩ የአዲስ አበባው የእነ አስማረች ታሪክ የፈጠራ ስለሆነ ፊት ለፊት መግጠም አትችልም። የጽሑፍ ችሎታ ካለህ ደግሞ ልቦለድ መጽሐፍ ጽፎ ትውልድንም ማስተማር፣ ማዝናናት ብሎ ም እራስን መጥቀም ይቻላልና በዚያ መስመር ጸሐፊውን ያስቡበት እላለሁ።

      Delete
  8. ሌባን ሌባ ካላልከው ሌብነቱ አይታወቀውም። ታደሰ የሲያትል ገብርኤል ቤተ ክርስቲያንን ከመከፋፈል እና ገንዘቧን ከመዝረፍ ባሻገር፤ ከሴት ጋር ሲሞካሞክ ነው የሚታየው። እያምታታ ከሚኖር ለምን ሚስቱን እና ልጁን አምጥቶ ኑሮውን በሰላም አይኖርም። እኛ እናውቃለን፤ ይኼ ጽሑፍ ከመውጣቱ በፊት ስለ ታደሰ ማንነት በደንብ እናውቃለን። በጣም ሲበዛ እግዚአብሔርን የሚዳፈር ባለጌ ሰው ነው።
    የሚገርመው ነገር ሲያትል ገብርኤል ካሉት አባቶች ጋር የሚያዘወትሩት ሴቶች በሙሉ ባላቸውን የፈቱ ናቸው። ታደሰም እነዚህን ፈቶች ሲሞካሞክ ነው የሚታየው ምናልባትም፤ ማታ ማታ እያደረጋቸው ይሆናል እንጂ፤ ገዳም ተብሎ ሴት የሚበዛበት ቤት አይተንም ሰምተንም አናውቅም። ለታደሰ ግን ይመቸዋል ባላቸውን የፈቱትን ቦዘኔዎች የናፈቃቸውን ያህል አንድ በአንድ ይደስቃቸዋል ። ይቅርታ ይደረግልኝ እኔ ታደሰን አላምነውም፤ ወልፋቸውን በተራ እየተወጡም ይሆናል፤ ታደሰ በፍጹም አይታመንም፤ ገዳም እየተባለ ቤት ውስጥ ባሎቻቸውን የፈቱ ጥመኞች የሚዉሉበት ነው። በየትኛው ገዳም ነው ሴቶች ለወሬ፤ ለስላቅ፤ ለሕሜት፤ ለነገር፤ ገዳም ድረስ ተኪዶ የሚመጣው፤ ለማንኛውም ታደሰ ምግባርህን አስተካክል፤ ቅዳሴ ይቅርብህ፤ ፈጣሪህን ይቅርታ ጠይቅ

    ReplyDelete
  9. heyyyyyyy. let him mess around with those women. let him do what he wants. if he wants to work his shit with women then let him be. damn man. he is a pimp. let him do his thing . it seems like you are jealousyyyyyyyyyyyyy. this is his time to f**around niggge

    ReplyDelete
  10. መሳቂያ!! ሞት ይሻላል እንዲህ ከመዋረድ

    ReplyDelete
  11. Hey where is next part??? lebwoled new ende derasiwen ena directerun yemitebik????

    ReplyDelete
  12. when is the next part??/ ahunis metebeku selechegn>>>>>>>

    ReplyDelete
  13. Yea me too metebeku selechegne???????????????????????

    ReplyDelete
  14. ጸሐፊው ምነው ታሪኩ እዚህ ላይ አለቀብህ እንዴ ? ወይስ ያ ረጅም እጁን አሳረፈብህ? ታደሰ እጁ ረጅም ነው ወዳጄ........

    ReplyDelete
  15. We have been waiting so long can you finish the story about his ass

    ReplyDelete
  16. I think the writer is on vacation.....New weyis tariku alekebih?

    ReplyDelete
  17. እስኪ እንታገስ። ጸሐፊውን እያስለመኑት ሳይሆን አይቀርም። ስለዚህ ጸሐፊው ጊዜውን መስዋእት አድርጎ እስኪጽፍ ድረስ በትዕግስት እንጠባበቅ። ግን እባክህን እየጠበቅን ነው ጸሐፊውም ብትሆን ተሎ ጻፍልን የዚህን ሰው ታሪክ ለማወቅ ጓጉተናል።

    ReplyDelete
  18. i would like to know more about this mother fucker

    ReplyDelete