ቀን ግንቦት 11፣ 2005 ዓ.ም
May 19, 2013 G.C
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
“እግዚአብሔርን ያይደለ እናንተን ልንሰማ በእግዚአብሔር
ፊት ይገባልን? እስኪ እናንተ እራሳችሁ ፍረዱ። እኛ ያየነውን እና የሰማነውን ነገር ከመናገር ዝም እንል ዘንድ አንችልም” ሐዋ
4፤19
ለብጹዕ አቡነ ሉቃስ የሲያትል መካነ ብርሃን ቅዱስ
ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሊቀጳጳስ እና ለመካነ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን
አስቀድመን የ እግዚአብሔር ሰላም ከሁላችን ጋር
ይሁን እያልን ሁላችሁም እንደምታውቁት እና በተደጋጋሚ እንደገለጽነው ደጉ አባታችን ለቀ ጳጳስ አቡነ ዜና ማርቆስ ካረፉ በኋላ የቤተክርስቲያናችን
አስተዳደር ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበላሸ እና መፍትሔ እያጣ መምጣቱን በዚህ መልኩ ለምዕመናን ለመግለጽ እንወዳለን።
በነሐሴ 21፣ 2003 ዓ.ም ደጉ አባታችን ሊቀ
ጳጳስ አቡነ ዜና ማርቆስ ያሰመጡልን መምህራችን አባ ገብረሥላሴ ጥበቡ ያለአግባብና በግል ጥላቻ ከቤተክርስቲያናችን መወገዳቸውን
ተከትሎ አጠቃላይ ያለውን የቤተክርስቲያናችንን ችግር መፍትሔ እንዲያገኝ ተሰባስበን የጠየቅነውን ጥያቄ እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ያለምንም
መፍትሔ ሁለት አመት ሊያስቆጥር ጥቂት ወራት ቀርተውታል። ይህንን
ደብዳቤ ለመጻፍ የተነሳንበት ዋና አላማ ባለፈው በመስከረም 23፣ 2005 ዓ.ም ምዕመናኑ ተሰባስቦ የመጨረሻ መፍትሔ እና ሙከራ
እንዲያደርጉ ከዚህ በፊት የመረጥናቸውን 13 ሽማግሌዎች ወደ ብጹዕ አቡነ ሉቃስ ፊት ቀርበው እንዲነጋገሩ ተልከው ነበር በዚህም
መሰረት ሽማግሌዎቹ ከብጹዕ አቡነ ሉቃስ ሊቀ ጳጳስ ጋር ተገናኝተው ጉዳዩን እሳቸው በሾሟቸው ሰዎች አማካኝነት እንደሚወያዩና መፍትሔ
እንደሚሰጡ ባዘዙት መሰረት በህዝብ የተመረጡት ሽማግሌዎች የሊቀጳጳሱን ቃል አክብረው እሳቸው ካስመረጧቸው ሰዎች ጋር በተደጋጋሚ
ተነጋግረዋል። በውጤቱም ምዕመኑ በቤተክርስቲያኑ ጉዳይ ምንም እንደማይመለከተው እና የነሱ ስራ የተጣላ ሰው ካለ ማስታረቅ ብቻ እንደሆነ
አሳውቀው ሽማግሌዎቻችንን አሰናብተዋል።
እኛም ይህንን ውሳኔያቸውን በሚመለከት እንደማንስማማ
ምዕመኑ የቤተክርስቲያኑ ባለቤት እንደሆነ እና ማንኛውም ጉዳይ ስርዓቱን ጠብቆ ማወቅ መረዳት እንዳለበት ለዚህም ሊቀጳጳሱ አቡነ
ሉቃስ ሐላፊነት እንዳለባቸው የሚያስገነዝብ ሁለት ገጽ ደብዳቤ መጋቢት 24፣ 2005 አስገብተናል። አያይዘንም ምዕመኑ ሰብስበው መፍትሔ እንዲሰጡ ጠይቀናል። ይሁን እንጂ ሊቀ
ጳጳሱ አቡነ ሉቃስ እስከዚህ በፊቱ የምዕመናኑን ጥያቄ ችላ በማለት በህዝቡ ስም ያለ ምዕመኑ እውቅና የተለያዩ ስራዎችን እያደረጉ
ይገኛሉ። ይባስ ብለው ባለፈው ሳምንት ያለ ምዕመናኑ እውቅና እና
ተሳትፎ ቦርድ ኦፍ ትረስቲ አቋቋሙ። ከዛም በፊት እ ኤ አ በጃንዋሪ
20፣ 2013 ምዕመናኑ ባልተሰባሰበበት እና በማያውቀው ጉዳይ ሁለት ሶስተኛው አባል ተሰባስቦ ፈርመዋል ተብሎ ምዕመናኑ የማያውቀው
መተዳደሪያ ደንብ መሻሻያ እንደተደረገበት የሚያሳውቅ ወረቀት በጃንዋሪ 22፣ 2013 ኦሎምፒያ ተመዝግቦ ይገኛል። (ይህንን የመሳሰሉ
ምዕመናኑ ሳያውቀው በስማቸው ተፈርሞ ኦሎምፒያ የገባ ብዙ ዶክመንት በእጃችን ይገኛል። ዛሬ በአውደ ምሕረቱ ተገኝተን ጥያቄያችንን
ይመለስልን ከማለታችን በፊት ብዙ መንገድ ተጉዘናል፤ ጥቂቶችም እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል።
·
ደጉ አባታችን ሊቀ ጳጳስ አቡነ
ዜና ማርቆስ ያሰቀመጡልንን የወንጌል መምህር በግል በተፈጠረ ጠብ ከቤተክርስቲያን አገልግሎት ሲይስወግዱ በነሐሴ 21፣ 2003 ዓ.ም
በቅዱስ ሲኖዶስ ካሉት ሁለት ሊቃነ ጳጳሳት እና ሊቀ ካህናት ሽምግልና በመላክ ሠላም እንዲፈጠር ጥረናል።
·
በሊቃነ ጳጳሳቱ የተሞከረው
ሰላም ባለመምጣቱ አባታችን አቡነ ሉቃስ ልጆቻቸውን አይንቁም በሚል የሚያስታርቁ ብጹዓን ናቸው ብለን ሰላም እና እርቅ እንዲመጣ
በመስከረም 28፣ 2004 ዓ.ም ለእርሳቸው እና ለቤተ ክርስቲያኑ ቦርድ ደብዳቤ አስገብተናል።
·
በጥቅምት 12፣ 2004 ዓ.ም
እርሳቸው ከእኛ ጋር ለመነጋገር ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ከቤተ ክርስቲያን ቦርድ አባላት ጋር በመነጋገር ችግሩ አስተዳደራዊ መሆኑን
ተገንዝበናል።
·
በጥቅምት 19፣ 2004 ዓ.ም
ለእርሳቸው እና ለቦርዱ አባላት አጠቃላይ የምዕመናኑ ብሶት ዘርዝረን መፍትሔ እንዲሰጠን በ4 ገጽ ደብዳቤ ጠይቀናል
·
እ ኤ አ በጥቅምት 22፣
2010 እርሳቸው ከእኛ ጋር ለመነጋገር ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ቅ/ሲኖዶስ በሊቀ ጳጳስ አቡነ መልከ ጼዴቅ በተጻፈ ደብዳቤ የቤተ ክርስቲያኑ
የበላይ ጠባቂ አድርጎ በሾሟቸው መሠረት እኛም የተለያየ ችግር እንዳለብን የሚያስውቅ ደብዳቤ እና ወኪል በሕዳር 3፣ 2004 ዓ.ም
ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ ልከናል። ቅዱስ ሲኖዶሱ መፍትሔ ባለመስጠቱ ባሻገር
ወኪላችንን ሊቀ ጳጳሱ አውደ ምሕረቱ ላይ በመሆን ከፍተኛ ሞራልና ልብ የሚነካ እጅግ አሳዛኝ የሆኑ ቃላትን ሰንዝረዋል።
·
ቅዱስ ሲኖዶስ ምንም መፍትሔ
ስላልሰጠን እና ችግራችንን ስላልሰሙን በታህሳስ 16፣ 2004 ዓ.ም የደረስንበትን ጉዞ እና አጠቃላይ አካሄዳችንን በአጭሩ ለምዕመናን
በበራሪ ወረቀት አሳውቀናል።
·
በየካቲት 18፣ 2004 ዓ.ም
ምዕመናኑ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ባለ አዳራሽ በመሰብሰብ የደረስንበትን አሳውቀን 13 አባላት ያሉበት የቤተ ክርስቲያን ታላላቅ ሰዎችን
ያካተተ ሽማግሌ ሕዝቡ መርጦ ጉዳዩ በሰላም እንዲፈታ ወደ እርሳቸው ሽምግልና ልከናል፤ ከቦርድ አባላት ጋርም ተነጋግረናል።
·
በቅዱስ ሲኖዶሱ ተስፋ ያልቆረጠው
ምዕመን በአመት ሁለት ጊዜ በሚካሄደው መደበኛ ስብሰባ መፍትሔ እንዲሰጠን በተደጋጋሚ ደብዳቤ ልከናል፤
·
በያዝነው አመት መስከረም
23፣ 2005 ዓ፣ም ም ዕመናኑ የወከላቸው ሽማግሌዎች ለመጨረሻ ጊዜ እንዲያናግሩ ልከናል
ይሁን
እንጂ ለተጠየቅነው ጥያቄ በአግባቡ መልስ ሳይሰጠን እና ወደ ጎን በመተው በጹዕ አባታችን አቡነ ሉቃስ ሊቀ ጳጳስ ያለ ምዕመኑ እውቅና፤
1.
ቤተ ክርስቲያናችንን ወደ ገዳምነት
ቀይረዋል፤ ምንም እንኳን ገዳም በመሆኑ ምንም ተቃውሞ ባይኖረንም፤ ገዳም በመሆኑ ምን እንደምንጠቀም፤ ምን እንደምናገኝ እና እንደምናጣ
ካለማወቃችን ባሻገር የምዕመኑ ጥያቄ እንደሆነ ተደርጎ ለቅዱስ ሲኖዶስ መቅረቡና ም ዕመናኑ ተስማምቶበት ያጸደቀው ነው ተብሎ ያለ
ምዕመናኑ እውቅና ኦሎምፒያ መዝገብ ቤት መግባቱ አሳዝኖናል፤
2.
እንዱ ጥያቄያችን በቤተ ክርስቲያናችን
በሚደረገው የአገልግሎት ምርጫ ምዕመኑ የአባልነት መብቱ ተጠብቆ ይምረጥ ይመረጥ ቢሆንም በተቃራኒው ምዕመናኑ ሳይሳተፍበት የተለያዩ
የኮሚቴ ምርጫ የተካሄደ ሲሆን በተለይም ያለፈው ሳምንት የተሾሙት ቦርድ ኦፍ ትረስቲ በጣም የሚያሳዝን ሆኖ እግኝተነዋል፤ በመሆኑም
በዛሬው ዕለት በዓውደ ምሕረቱ ቆመን በድጋሚ እስካሁን ጥያቄያችንን መልስ እንዲሰጠው እንጠይቃለን፤ ጥያቄዎቹም ባጭሩ አስቀምጠነዋል።
·
ቤተ ክርስቲያናችን እንደማንኛውም
በሰሜን አሜሪካ ሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ ስር እንደሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት በቅዱስ ሲኖዶስ ሕግና ስርዓት ትመራ
·
በቤተ ክርስቲያናችን እንደሚታወቀው
የመተዳደሪያ ደንቡ ምዕመኑ ስለለለው መብቱን እና ግዴታውን ስለማያውቅ፤ እንዲያውቅ እና እንዲረዳ፤ መምረጥ ሆነ መመረጥ መብቱ እንዲጠበቅ፤
·
በመተዳደሪያ ደንቡ እንደተጠቀሰው
እና እንደሚያዘው የሰበካ ጉባኤ አባላትም ይሁን የቦርድ አባላት ወይም የቦርዶ ኦፍ ትረስቲ አባላት አገልግሎት ዘመን እንዲኖራቸው
እና የአገልግሎት ዘመናቸው ሲያልቅ ሌሎች አገልጋዮች በምትካቸው በምልዐተ ጉባኤ እንዲመረጥ፤
·
በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት
ቤተ ክርስቲያናችን የኦዲት እና ቁጥጥር ኮሚቴ ተመርጦ አጠቃላይ የሒሳብ እና ንብረት ምርመራ እንዲደረግ፤
·
በምዕመናኑ ስም እና ገንዘብ
የተሰሩ ስራዎች በጥቂት ለሰቦች እንዲሰሩ ተደርጎ የሚቀርቡ ስራዎች እንዲወገዱና የህዝብ ባለቤትነት እንዲረጋገጥ እንዲሆን፤ ለዚያ
ማሳያ ባለፈው በደጉ አባታችን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ዜና ማርቆስ ስም በተሰራው መታሰቢያ ሕንጻ የተቀመጠው ድንጋይ ላይ ቤተ ክርስቲያኑን
ገንብተው በጉልበትም በገንዘብም እዚህ ያደረሱትን ምዕመናን ከኛ ጋር ይሉትም ሆነ በሕይወት የሌሉትን ዘንግቶ የጥቂት ግለሰቦች ስም
መቀመጡ ያደባባይ ምስጢር ነው።
·
ሁሉም ምዕመናን እንደ ቤተ
ክርስቲያን ልጅነታቸው ማግኘት የሚገባቸው አገልግሎት ያለምንም አድሎና መድሎ ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ እንዲደረግ፤ በተቃራኒው
አንዱ እንደ ልጅ ሌላው እንደ እንጀራ ልጅ በመታየት ሊባርኩን በያዙት መስቀል አንዱን ሲያሳልሙት አንዱን ሲነሱት፤ ከልጆቹና ከራሱ
ጉሮሮ ነጥቆ በሰራው ቤተ ክርስቲያን አንዱ ስለቱን ሲለምን ሌላው ስለቱን አትለምንም ሲባል፤ ለበረከት አገልግሎት ሊሰጥ ተገፍትሮ
ውጣ ሲባል፤ ክርስትና ለማስነሳት፤ ፍትሐት ለማስፈታት፤ በተክሊል በስጋ ወደሙ ለመጋባት እና የድጋፍ ደብዳቤ ለማግኘት አግባብ የሌለው
የገንዘብ ተመን ከአቅሙ በላይ የተጠየቀ ምዕመን ቤቱ ይቁጠረው።
·
ቤተ ክርስቲያናችን የተደራጀ
የሰንበት ትምህርት ቤት ስለለለው አጠቃላይ ወጣቱ፤ ሕጻናቱን እና ሀገር ተረካቢውን ትውልድ የሚያካትት ሰንበት ትምህርት ቤት እንዲቋቋም
የሚሉ ሲሆን፤
እነዚህን ጥያቄዎች
መጠየቃችን እንደነውር ተቆጥሮና ሌላ ስም ተሰኣጥቶት እስካሁን ድረስ መልስ ሳይሰጠን ቆይተናል፤ በአንጻሩ የዋሁን የቤተ ክርስቲያናችንን
ምዕመን በቡድን በመከፋፈል እና የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ይህንን ጥያቄ የሚጠይቁትን ምዕመናንን ፤
1.
አባቶችን ሊያባርሩ ቤተክርስቲያኑን
ሊወርሱ የተቋቋሙ ናቸው እያሉ የከሱናል፤
2.
የተወሰኑ ክፍለ ሐገር ሰዎችን
በመጥቀስ ከዚህ ቦታ እንደዚህ ያለውን ክፍለ ሐገር ለማስወገድ የተነሱ ናቸው ብለው የሐገራችን ወቅታዊው መንግስት የሚጣእቀምበትን
የመከፋፈል መንገድ እየተጠቀሙ ሊከፋፍሉን ይሞክራሉ፤ እኛ ግን በጎሳና በዘር ሳይሆን በአንድ የቤተክርስቲያን ልጅነት እና በኢትዮጵያዊነት
እናምናለን።
3.
ቤተ ክርስቲያኑን ለግለሰብ
ሊያስረክቡ የተነሱ ናቸው ይሉናል፤ ነገር ግን እነሱ እንደምያስቡት ሳይሆን ከላይ የዘረዘርናቸው ጥያቄዎች እንዲመለሱ የምንፈልግ
ምዕመናን መሆኑ ታውቆ ጥያቄያችንን እንዲመልሱ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
እግዚአብሔር አምላካችን ለቤተክርስቲያናችን ሰላሙን እንዲሰጠን የዘወትር
ጸሎታችን ነው።
የምዕመናን ተወካዮች
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
የመድኃኒት ንግድ ሥራዬን ለማስፋፋት በተጠቀምኩበት ብድር ለመርዳት ሚስተር ቤንጃን ከሚያስፈልጓቸው በላይ አልፈዋል ፡፡
ReplyDeleteእነሱ ለመስራት ወዳጃዊ ፣ ባለሙያ እና ፍጹም ዕንቁዎች ነበሩ ፡፡ እኔ ለማነጋገር ብድር የሚፈልግን ማንኛውንም ሰው እመክራለሁ ፡፡ Lfdsloans@outlook.com.WhatsApp ... +19893943740.