Monday, 10 June 2013

የሲያትል ገብርኤል ካህናት ወንጌሉን እያስተማሩበት ነው ወይስ እየነገዱበት?


 
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን::
“እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል” የሚባል የአባቶች አነጋገር አለ:: እንደተደበቁ መቅረት፤ እንደተሸፋፈኑ መቆየት፤ እንዳወናበዱ መቀጠል አይቻልም:: አንድ ቀን ያበቃለታል:: በጨለማ የዶለቱት በብርሃን ይወጣል:: በጓዳ የዶለቱት ኽሳሎን ብቅ ይላል::እንኳን ከህዝብ በስተጀርባ ይቅርና ከጓደኛ የሸሸጉት አፈትልኮ ያመልጣል:: እነሆ እውነቱ በሲያትል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ገሃድ ሆነ::
የሲያትል ቤተ ክርስቲያን ሃላፊ ስመ ጥሩ የሆኑትን ተወዳጅ መምህር አባ ገብረ ሥላሴ ጥበቡን ከአቡነ መልከ ጸዲቅ ጋር በመተባበር ከሲያትል ማባረራቸው ይታወቃል:: በዚህም ምክንያት የሲያትል ወጣትና ሕዝቡ ቅር ተሰኝቶ መምህር ገብረ ሥላሴ ጥበቡ ወደ ቦታቸው እንዲመለሱ ቢጠይቅ ሃላፊው “ምን እንዳትሆኑ ነው” ብለው አሻፈረኝ አሉ:: እንደራሳቸው የግል ካምፓኒ ሽምግልና አልፈልግም አሉ:: በዚህ ምክንያት የቤተ ክርስቲያኑ ታዛቢ ምእመናን ሶስት ደብዳቤዎች ጽፈን ተማጸንናአቸው:: ሃላፊው ግን ወይ ፍንክች የአባ ቢላዋ ልጅ አሉ:: ይቀጥላል…

2 comments:

  1. የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ። ማቴ 11:15

    ReplyDelete
  2. ለቤተክርስቲያኑ ቦርድ፣ ካህናቶች፣ ስለ ሕንፃ መሰራት እና ማን ምን ማስተዳደር እንዳለበት፤ እንዲሁም መረሳት የሌለበት በካህናቶች የውስጥ ጉዳይ፤ እንዲሁም....

    ReplyDelete