ታደሰ የኋላእሸት አለምነህ የአሁኑ መላከ ብርሃናት ገብረስላሴ የኋላሸት አለምነህ ማን ነው?
ይሕ መልእክት ዘለፋ አይደለም...እውነታነት ያለው ታሪክ ነው።
ይሕ መልእክት ዘለፋ አይደለም...እውነታነት ያለው ታሪክ ነው።
ክፍል አንድ
.
እርግጥ ነው
አሁን ታደሰ የ56 አመት ሰው ነው። መቼም ወጣት ለመምሰል የማያደርገው ጥረት የለም፤ ልክ እንደ ወጣት ሴት፤ እዩኝ….
እዩኝ….. እንደምትል ኮረዳ፤ ያሳደገውን ጺሙን ጥቁር ቀለም እየቀባ ወጣት ሲመስል፤ አንዳንዴ ደግሞ ይሰለቸዋል መሰል ነጭ ጢሙ
ዥርግግ ብሎ ሲታይ…. ብቻ ያሳፍራል…. የጺሙ ሁኔታ ዚብራ ይመስላል። ወደ ታሪኩ ልውሰዳችሁ።
ከዚህ ፎቶ ግራፍ ላይ ደግሞ፤ አሜሪካ የዛሬ 2 አመት በዚሁ ቅዱስ ገብር ኤል ሲያትል ደብር ላይ አመንኩሱኝ አለም በቅቶኛል በማለት የምንኩስና ማዕረግ ከተቀበለ በኋላ.... መነኩሴ መስሎ ሲቀድስ ፤ጅብ በማያውቁት ሃገር ሄዶ ቆርበት አንጥፉልኝ ይላል አሉ...ወይ ማጭበርበር፤ ነገር ግን ከአንድ ሴት በላይ የሄደ ሰው ካህን ሆኖ መቀደስ ይችላል? መልሱን ለ እናንተ እተወዋለሁ...ታሪኩን ተከታተሉ...
ታደሰ የኋላእሸት አለምነህ ጥር 14 ቀን 1949 ዓ.ም በደብረታቦር አውራጃ ተወለደ። እርሱም ለቤተሰቡ የ3ተኛ ልጅ ነው።
ሁለት ታላላቅ እህቶች አሉት። 4 ወንድሞችም አሉት። ከወራቶች በፊት ኢትዮጵያ ቤተሰቦቼን ለመጠየቅ ከሁለት ጓደኞቼ ጋር ሄጄ
በነበርኩበት ወቅት፤ ለአንድ ዓላማ ጉዳይ ደብረታቦር ሄጄ ነበር፤ የታደሰን ቤተሰቦች ደግሞ በዚሁ አጋጣሚ ተዋወቅን፤ ከወንድሞቹ አንዱን ይርጋለም የኋላእሸት
አለምነህን ስለ ታደሰ ታሪክ አነጋግረነውም ነበር። እንደ ታደሰ
ታናሽ ወንድም ይርጋለም አገላለጽ፤ ታደሰ ከቤተሰባችን ከወንዶች መካከል በእድሜ ታላቁ እሱ ነው፤ ነገር ግን
ወላጆቹን በጣም ያስቸግር ስለነበር፤ አባታችን…. ታደሰን ይሄ ልጅ ገና ከአሁኑ ነገረኛና ቂመኛ ከሆነ ሲያድግ ማንም አይችለውም
በማለቱ በ7 አመቱ አያታችን ያሳድገው ዘንድ ተሰጠ። ከዚያም ከአያቶቹ ጋር መኖር በጀመረበት ወቅት፤ ከጎረቤት ልጆችጋር እየተደባደበ፤ እየተሰዳደበ፤ ድንጋይ እየተወራወረ ሲያስቸግራቸው፤ አያታችንም ቢገርፉትም ባህርይው አስቸጋሪ ሆኖ ስላገኙት፤
ድንገት ይሻሻል ይሆናል ብለው በማሰባቸው ምክንያት፤ በ16 ዓመቱ ቤተ ክርስቲያን ግብረገብ እንዲማር ተደረገ።
ይበልጡኑን ክፋትንና ተንኮልን ጨምሮበት ከቆሎ ተማሪዎች ጋር እየተደባደበ ሲያስቸግር፤ እስኪ
ልዳረው....... ያን ጊዜ ትንሽ ሰከን ይላል፤ ልጅነትም ይቀራል፤ በማለት በ18 አመቱ አንዲት ትንሽዬ የ14
አመት ትዕግስት ፈረደ ከምትባል ልጅ ጋር ወላጆቹ እና አያቱ አጋቡት። የታደሰ ወላጆቹ ገበሬዎች ነበሩና፤ በወላጆቹ
እየተረዳ እስከ 21 አመቱ ድረስ ከልጅቷ ጋር አብረው 3 አመት አንድ ቤት ውስጥ ይኖሩ ነበር። ትዳራቸውም ደርቶ እንደነበርና
አንዳንዴ ይደበድባት እንደነበርም ይርጋለም አጫውቶናል። በተጨማሪም እንደ ይርጋለም አገላለጽ፤ የታደሰ ባለቤት በልጅነቷ አርግዛ በወሊድ ምክንያት ልጇም እሷም አብረው እንዳረፉ፤ ታደሰ ደግሞ በተፈጠረው ሁኔታ እንደተጎዳ እና ከመጠን በላይ እንዳዘነ
ነግሮናል። በዛን ወቅት ታደሰ እና ባለቤቱ የሚኖሩትም በገጠር ስለነበር፤ ባለቤቱን ሆስፒታል ለመውሰድ ጥረት ቢያደርግም፤ በጊዜው ሕክምና ባለማግኘቷ ምክንያት ሕይወቷ በቀላሉ ሊያልፍ ቻለ። ታደሰ የሚችለውን ያህል ጥረት አድርጎ ሳይሳካለት በመቅረቱ፤ ባለቤቱንና ሳይወለድ የሞተውን ልጁን ሳያይ፤ ሁለቱም በመሞታቸው ምክንያት ታላቅ ሃዘን ላይ ነበር።
በአንድ ጊዜ ሁለት ሰው ማጣት ከባድ ቢሆንም፤ ታደሰ በሃዘን ምክንያት ተጎድቶ ስለነበር፤ ወላጆቹም የሱን ትካዜና ሃዘን ማየት ስላልፈለጉ፤ ከቦታው
እንዲርቅ በማለት አዲስ አበባ ካለው ወንድማቸው (ለታደሰ አጎት) ዘንድ እንዲቆይ እና ዘመናዊ ትምህርትም እንዲማር በሚል ሃሳብ ወደ አዲስ አበባ እንዲሄድ ተደረገ። ከተወሰነ ወራት በኋላ፤ አጎትዬው ታደሰን ከቤተክህነት ካሉት አባቶች ዘንድ አስተዋውቆ ቅድስት ስላሴ ካቴድራል አዲስ
አበባ፤ በዲቁና እንዲቀጠር አደረጉ። የዘመናዊ
ትምህርት ቤትም በአጎቱ አማካኝነት ተመዝግቦ ማታ ማታ መማር ጀመረ፤ ከዚያስ..........
በታደሰ የኋላእሸት ሕይወት ዙሪያ ከይርጋለም እና ጸሐይ ጋር ያደረግነውን ቃለ መጠይቅ እና ታደሰ የኋላእሸት
በአዲስ አበባ የነበረው ቆይታ እንዴት እንደነበር እመለስበታለሁ ተከታተሉን? ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብቶ በሚማርበት
ወቅትስ ምን ያደርግ ነበር? ይህን በሚቀጥለው ጽሑፌ እመለስበታለሁ ይጠብቁን….


ያሳዝናል። ይህንን ታሪክ ሰው ያምነናል ብላችሁ ማቅረባችሁ። የትኛው ወንድም ነው በወንድሙ ላይ እናንተ ያላችሁትን የሚናገረው? ኧረ እባካችሁ እናስተውል! የሚታመን ነገር እናውራ። አባ ገብረሥላሴን እንደ ቤተሰብ የሚያውቃቸው ብዙ ሰው መኖሩን አትዘንጉ።
ReplyDelete